በጉብኝቱ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦን ጨምሮ የተለያዩ ስራ ክፍል ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡ ድርጅቱ በአፋር ክልል ፣ኦሮሚያ ፣ጋንቤላ ፣ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ትግራይ ክልልና አዲስ አበባን ጨምሮ በትምህርት፣ በስርዓተ-ፆታ፣ በአድቮኬሲና የሰብዓዊ ድጋፍ ላይ ትኩርት በማድረግ የሚሰራ ድርጅት መሆኑን የ Development Expertise Center (DEC) ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ ደምሴ ገልጸዋል፡፡ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ ድርጅቱ በተለያዩ ዘርፎች ላይ የሰራቸውን ስራዎች አድንቀው የጉብኝቱ ዓላማም ድርጅቱ መሬት ላይ ያከናወናቸውን ተግባራት በመመልከት ለመደገፍ፣ከፕሮጀክቱም የተጠቀሙ ማህበረሰብ ክፍሎችን ሃሳብ ለመውሰድና በጋራ በክልሉ የሚሰሩ የመንግስት ተቋማትን አስተያየት ለመቀበል እንደሚረዳ አብራርተዋል፡፡ በቀጣይም ይህን አበረታች ስራዎችን በማጠናከር መንግስት ሊደርስባቸው የማይችሉትን ልማቶች ከማህበረሰቡ ጎን በመሆን አጠናክራችሁ መቀጠል ይኖርባችዋል በማለት ባለስልጣን መስርያቤቱም በተቻለው አቅም አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርግ አንስተዋል፡፡ በመጨረሻም የልማቱ ተጠቃሚ ማህበረሰብም በአካባቢው የተሰራውን ማንኛውንም ልማት በተገቢው መንገድ በመንከባከብ መጠቀም እንዳለበት በአካባቢው በጉብኝቱ ወቅት ለተገኙ የመንግስት ሃላፊዎችና የልማቱ ተጠቃሚ ማህበረሰብ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ፡፡