የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን አመራሮችና ሰራተኞች “ሴትን አከብራለሁ ጥቃቷንም እከላከላለሁ” በሚል መሪ ቃል ዓለም አቀፍ የፀረ ፆታ ጥቃት ቀንን በደመቀ ሁኔታ አከበሩ፡፡ በበዓሉ ላይ የተገኙት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ እንዳሉት በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ፆታዊ ጥቃት ለመከላከል በአመት አንድ ጊዜ ብቻ መወያየት ሳይሆን የሁልጊዜ ተግባራችን መሆን እንደለበት ተናግረዋል፡፡ አክለውም ሴቶችን በሁሉም መስኮች በማሳተፍ ብቃታቸውን መጠቀም መቻል አለብን ሲሉ ገልጸዋል፡፡ ሴቶችን የማክበር አንዱ መገለጫ ጥቃቷን በመከላከል ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ከፆታዊ ጥቃት ነጻ የሆነ ተቋም በመፍጠር ለሌሎች ሞዴል መሆን አለብን ብለዋል፡፡ ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ safeguarding policy መውጣቱን ገልጸዋል፡፡ ይህን በዓል ስናከብር ባለፉት ሁለት አመታት በአገራችን በነበረው ጦርነት የጥቃት ሰለባ የሆኑ ሴቶቻችን አሁን በተደረገው የሰላም ስምምነት መሰረት ሰላማቸውን ባገኙበት ወቅተ መሆኑ ለየት ያደረገዋል ብለዋለ፡፡ አለም አቀፍ የፀረ ፆታ ጥቃት ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ31ኛ ጊዜ በአገራችን ደግሞ ለ17ኛ ጊዜ ተከብሮ ውሏል፡፡