የቻይና ፋዉንዴሽን ፎር ሩራል ዴቨሎፕመንት የኢትዮጵያ ቢሮውን እ.ኤ.አ በ2019 በአዲሱ አዋጅ የተመዘገበ ድርጅት ሲሆን በቀድሞዉ ስያሜ የቻይና ፋዉንዴሽን ፎር ፖቨርቲ አሊቬሽን በመባል ይታወቃል ነበር፡፡ የቻይና ፋዉንዴሽን ፎር ሩራል ዴቨሎፕመንት የኢትዮጵያ ቢሮ በሶስት ዓመት ቆይታዉ በርካታ ፕሮጀክቶችን መተግበር የቻለ ድርጅት ሲሆን ከነዚህም መካከል ከት/ት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የተማሪዎች ቦርሳ እና መማሪያ ቁሳቁሶች ከቻይና ሃገር እያስመጣ ድጋፍ ለሚያስፈልጋችዉ የመጀመሪያ ደረጃ ተማሪዎች በተለያዩ ክልሎች ሲያቀርብ ቆይቷል፡፡ በተጨማሪም የተማሪዎች ምገባ፣ ንጹህ የመጠጥ ዉሃ አቅርቦት ፣ የሴቶች ኢኮኖሚያዊ አቅም ማዳበር እና የምግብ ድጋፍ ስርጭቶችን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ የድርጅቱ 3ተኛ ዓመት የኢትዮጵያ ምስረታዉ ፕሮግራም ላይ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ድርጅቱ በርካታ እንግዶች በተገኙበት ጠቅላላ ሪፖርት ያቀረበ ሲሆን በዕለቱም ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦን ጨምሮ ከቻይና ኢምባሲ በኢትዮጵያ ፤የቻይና ቻምበር ኦፍ ኮሜርስ ፤ የቻይና ፋዉንዴሽን ፎር ሩራል ዴቨሎፕመንት ዋና ቢሮ ዳይሬክተር ዉ ፖንግ ፤ የግብርና ሚኒስቴር ተወካይ ፤የዉናሃ ኢነርጂ ሚኒስቴር ተወካይ ፤የገንዘብ ሚኒስቴር ተወካይ እና ሌሎች እንግዶች ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡