የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ከሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ አቃቤ ህግ ጋር በመተባበር በሲቪል ማህረሰብ ድርጅቶች አዋጅ እና በተለያዩ ህጎች ላይ የውይይት መድረክ አካሄደ፡፡ በመድረኩ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ በመክፈቻ ንግግራቸው እንዳሉት በአገር አቀፍ ደረጃ ባለፉት አራት ዓመታት የሪፎርም ስራዎች ሲከናወኑ እንደነበር በማስታወስ በዋናነት ሪፎርሙ ከህግ እና ከተቋማት ጋር የተያያዙ ሪፎርሞች መሆኑን አንስተዋል፡፡ ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ ደረጃ ሲያስወቅሳት የነበሩ ህጎች ህዝብን ባሳተፈ መንገድ ማሻሻል መቻሉን ገልፀው ከነዚህ መካከል የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት አዋጅ አንዱ ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡ ህግ ማሻሻል ብቻ ግብ አይሆንም ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ የተሻሻሉ ህጎች ልክና መጠን ስራ ላይ መዋል፣ ዜጎችን መጥቀም መቻል፣ አለበት እንዲሁም መሬት ላይ ወርዶ የዜጎችን መብትና ጥቅም ማዳበር መቻል አለበት ሲሉ ገልፀዋል፡፡
ሌላው ያነሱት ባለስልጣን መስሪቤቱ ከፍተኛ የሆነ የሪፎርም ስራዎች ሰርቷል በተለይ ለህዝብ ቅርብ እንዲሆን የሲቪል ማህረሰብ ድርጅቶች ለአገር ግንባታ፣ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ እና ለልማት የሚያደርጉትን አስተዋጽኦ በሚገባ መወጣት እንዲችሉ ለማድረግ መቻሉን ገልፀዋል፡፡ በሶስት ዓመታት ውስጥ በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የተመዘገቡ አዲስ ድርጅቶች ከ2500 በላይ ነው በማለት ይህ ቁጥር በቀድሞ አዋጅ በአስር ዓመትታ ውስጥ ያልተመዘገበ ውጤት ነው ሲሉ አብራርተዋል፡፡ በመጨረሻም በፌደራል ደረጃ ከፍተኛ ሪፎርሞች ቢደረጉም በሚፈለገው ደረጃ ወደክልል የማውረድ ስራ አልተሰራም ይህንንም በቀጣይ ለመስራት በጋራ መቆም አለብን በማለት ባለስልጣን መስሪያ ቤቱም ለክልሎች እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡