የሲቪል ማህረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ለሁለተኛ ዙር በማህበራዊ ተጠያቂነት ላይ ስልጠና ሰጠ፡፡ በስልጠናው ላይ የተገኙት የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ እንዳሉት መስሪያ ቤቱ ባለፉት ዓመታት በለውጥ ሂደት ውስጥ መሆኑን አንስተው በዋናነት የተቋሙ ሰራተኞች አቅማቸውን ለማጎልበትና የአመለካከት ለውጥ ማምጣት እዲችሉ፣ የአገልግሎት አሰጣጡን የተሻለ ለማድረግ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን መስጠቱን ገልፀዋል፡፡ አያይዘውም አዋጅ 1113/2011 ሲወጣ በነፃነት የተደራጀ የነቃ ማህበረሰብ ለመፍጠር ጠንካራ የሆነ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን መገንባት አስፈላጊ ነው ይህ ሲሆን ግዴታውን የሚወጣ ማህበረሰብ መፍጠር ይቻላል ብለዋል፡:
የዛሬው ስልጠና የማህበራዊ ተጠያቂነት ፕሮግራም አንዱ የተቋማችን የለውጥ አካል ነው፡፡ ሁሉም አመራርና ባለሙያ በማህበራዊ ተጠያቂነት ላይ በቂ እውቀትና ግንዛቤ ሊኖረው እንዲሁም የስራው አካል አድርጎ መጠቀም አለበት በማለት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ማህበራዊ ተጠያቂነትን ተረድተው እንዲሰሩ አቅማቸውን መገንባት ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል ፡፡ ም/ዋና ዳይሬክተሩ አጽንኦት ሰጥተው የተናገሩት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች መንግስት ተጠያቂነት ፣ግልጸኝነት እና የመልካም አስተዳደር ችግር አለበት ብሎ ለመናገር በመጀመሪያ ራሳቸው ሞዴል መሆን አለባቸው ሲሉ ተናግረዋል፡፡