ንቁ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ለሰላም፣ለዲሞክራሲና ለልማት በሚል መሪ ቃል ለ2ተኛ ግዜ ዛሬ በሒልተን ሆቴል ተጀምሯል፡፡ ኤግዚቪሽኑን ዶ/ር ጌዲዬን ጢሞቲዬስ የፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትሩን ጨምሮ ሌሎች ሚኒስትሮች፣ኮሚሽነሮች፣የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ተወካዬች፣የተለያዩ የግል ሴክተሮች እና በርካታ እንግዶች በተገኙበት ተከፍቷል፡፡ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሳምንት ከዛሬ ጀምሮ አስከ ቅዳሜ ሰኔ 25/2014 ዓ.ም ድረስ ይቆያል አርሶም መጥተው እንዲጎበኙ ጋብዘነዎታል፡፡