በአዋጅ ቁጥር 1113/2011 ተመዝግበው በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ወላይታ ሶዶ ከተማ እና አርባ ምንጭ ከተማ እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ ሶስት ድርጅቶችን የስራ እንቅስቃሴ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የስራ ሃላፊዎች በቦታው ተገኝተው ጎብኝተዋል፡፡ ጉብኝቱ በምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ የተመራ ሲሆን በክልሉ የሚንቀሳቀሱትን ዩሪያዲስ ቪሌጅ ኢትዮጵያ (uriyadis village Ethiopia) ፤ ቦሳጆ የበጎ አድራጎት ድርጅትን (bosajo charity organization)፣ የቢላቭድ ኢትዮጵያ እንዲሁም አናሲሞስ ችልድረንስ ቪሌጅ ኢትዮጵያ የተባሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በህጻናትና ማህበረሰብ አቀፍ ልማት ላይ የሰሩትን ስራ ተመልክተዋል፡፡ ድርጅቶቹ በጎዳና ላይ የሚገኙ ህጻናትን በማንሳትና በመደገፍ እንዲሁም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎችን በመደገፍ የትምህርት፣ የጤናና እንክብካቤ አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኝ በመስክ ምልከታው ለመረዳት ተችሏል፡፡