በማህበራዊ ተጠያቂነት ዙሪያ በአማራ ብሔራዊ ክልል ደብረታቦር ከተማ ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እና ባለድርሻ አካላት ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡ የስልጠናው ዓላማ ማህበራዊ ተጠያቂነትን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በዘላቂነት በፕሮግራማቸው አካተው እንዲሰሩት ለማድረግ እና ጠያቂ እና ሃላፊነቱን የሚወጣ ማህበረሰብ ለመፍጠር ነው፡፡ በመርሃ ግብሩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክልሉ የሲማድ ዘርፍ ተወካይ አቶ ሙሉጌታ መኩሪያ ስልጠናውን ላዘጋጀው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ምስጋናቸውን አቅርበው ከስልጠናው በኋላ በማህበራዊ ተጠያቂነት ዙሪያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እና የመንግስት አካላት ግንዛቤ በመያዝ ተግባራዊ ለማድረግ እንሰራለን ብለዋል፡፡በስልጠናው የማህበራዊ ተጠያቂነት ጽንሰ ሃሳብ፣በኢትዬጵያ አመጣጡን እና አተገባበር ዙሪያ እና በርካታ ርዕሰ ጉዳዬች ተነስተው ውይይት እየተደረገበት ሲሆን በቀጣይ በሁሉም ክልሎች ይሰጣል፡፡