በስልጠናው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ እንደተናገሩት በተለያዩ ግዚያት የምናገኛቸው ስልጠናዎችን ለሃገራችንም ሆነ ለተቋማችን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡ ሀገራችን ለዘመናት በድህነት ውስጥ የኖረች ነች ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ዕቅዶቻችንን በተገቢው በማስፈፀም ኢትዮጵያን አፍሪካዊት የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ በቁርጠኝነት መስራት ይጠበቅብናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ይህንን ለማስፈጸም ከሚያስፈልጉ ጉዳዮች መካከል ጤና መሰረታዊ መሆኑን አንስተው ጤና የሌለው ማህበረሰብ ስለሀገር ልማት ስለብልፅግና ድህነት ስለመቅረፍ ማሰብ አይችልም ብለዋል፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም በስራችን ውጤታማ መሆን የምንችለው ጤና ስንሆን ነው በማለት የዛሬውም ስልጠና ስለጤናቸው ግንዛቤ ያላቸው እና ውጤታማ ሰራተኞችን ለመፍጠር ነው ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡በመጨረሻም ይህንን ስልጠና ከተቋማችን ጋር በመተባበር በስነ ተዋልዶ ጤናና ቤተሰብ ዕቅድ ዙርያ ግንዛቤ እንዲኖረን ያደረጉንን MSI Ethiopia reproductive choices በተቋሙ ስም አመስግናለው ብለዋል፡፡