ባለስልጣን መስርያቤቱ ከተለያዩ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የተረከባቸውን ተሸከርካሪዎች ለተለያዩ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች አስተላለፈ፡፡ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በአዋጅ ቁጥር 1113/2011 አንቀፅ 84 ንዑስ አንቀፅ 4 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ከተለያዩ ድርጅቶች የተገኙትን ንብረቶች እንደአስፈላጊነታቸው በማጣራት ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ያስተላልፋል ቢሚል ተደንግጓል ፡፡ ይህንኑ መሰረት በማድረግ ከተለያዩ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የተረከባቸውን 4 ተሽከርካሪዎችን ለ ሜሪጆይ ኢትዮጵያ ፣አዲስ ህይወት አይነስውራን ማዕከል፣ለሲቪል ማሃንዲሶች ማህበር እና ለአፎምያ አረጋዊያን ማዕከል አስተላልፏል ፡፡
በንብረት ርክክቡ ወቅት የተገኙት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ንብረት አስተዳድር ክፍል ሃላፊ አቶ ሃይለማርያም እንደተናገሩት ተቋማችን ከተለያዩ ድርጅቶች የተገኙትን ንብረቶች ድጋፍ ለሚሻቸው ድርጅቶች እንዲወዳደሩ በማድረግ እና በመለየት ተሸከርካሪዎችን ማስረከብ እንደቻሉ ተናግረዋል ፡፡ ሃላፊው አክለውም ለድርጅቶቹ ባስተላለፉት መልዕክት ተሸከርካሪዎቹ ለያዛችሁት ዓላማ እጅጉን እንደሚጠቅማችሁ ተስፋ እያደረግን ተረክባችሁ ወደ ስራ ስትገቡ ከናንተ ድጋፍ የሚሹትን የማህበረሰብ ክፍል የበለጠ ለመደገፍ መስራት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል፡፡ በመጨረሻም ተቋሙ በቀጣይ ተመሳሳይ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ድርጅቶች በመለየት ንብረት የማስተላለፉን ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል ፡፡