ሜሪስቶፕስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ከተቋቋመ ከአስራ አምስት አመት በላይ የቆየ ድርጅት ሲሆን በአሁን ወቅት ስያሜውን ለውጦ ኤምኤስአይ ኢትዮጵያ ሪፕሮዳክቲቭ ቾይዝስ በማለት በስነተዋዶ ዙሪያ ህብረተሰቡን በማገልገል ላይ ያለ የበጎ አድራጎት ድርጅት ነው፡፡ የእለቱን የልምድ ልውውጥ መርሃ ግብር ያስጀመሩት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለሰልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ ባስተላለፉት መልዕክት በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችና በመንግስት እንዲሁም በግል ተቋማት የተቀናጀ ትብብር ነው ሃገራችንን መለወጥ የምችለው ሲሉ ገልፀዋል፡፡ የባለሰልጣኑ የማኔጅመንት አባላት የልምምድ ልውውጥ መደረጉ ጠቀሜታው የጎላነው ያሉት ዋና ዳይሬክሩ ይህ የልምድ ልውውጥ የጋራ ጥቅሞች አሉት ግንኙነታችን ግን መርህን መሰረት ባደረገ መልኩ ነው ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ በእለቱም ከኤምኤስአይ ኢትዮጵያ ሪፕሮዳክቲቭ ቾይዝስ ካንትሪ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አበበ ሽብሩ ስለ ድርጅቱ የተቋቋመበት ዓላማና ሰራ እንቅስቃሴ ለተሳታፊዎች ያቀረቡ ሲሆን በቀረበው ሰነድ ላይ ሰፋ ያለ ውይይትና አንዲሁም ተቋሙ የሚጠቀምባቸውን የአስተዳደር ስልቶችና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ልምዶችን ከሁለቱም ተቋማት ለመጡት ተሳታፊዎች አቅርበዋል፡፡

በተመሳሳይ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለሰልጣን የክትትልና ድጋፍ ቡድን 2 ባለሙያ የሆኑት አቶ አድማሱ ታምራት በመስክ ምልከታቸው ኤምኤስኢን ድርጅት በተለያዩ ቦታዎች የሚሰራቸውን የስራ እንቅስቃሴ አጠቃላይ ሪፖርት ለተሳታፊዎች ያቀረቡ ሲሆን በሪፖርቱም ኤምኤስኢ ድርጅት በኢትዮጵያ ክልሎች ህብረተሰቡን የሚጠቅሙ ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየሰራ መሆኑን አብራርተዋል ፡፡