ይህም የተባለው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ለአመራሮቹና ባለሞያዎች በማህበራዊ ተጠያቂነት ዙርያ በካፒታል ሆቴል ስልጠና በተሰጠበት ወቅት ነው፡፡
ስልጠናውን የሚሰጡት ከገንዘብ ሚኒስትር እና ከዓለም ባንክ በመጡ ባለሞያዎች ነው ፡፡
የስልጠናውን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ ባስተላለፉት መልዕክት ተቋማችን የማህበረሰብ ተጠያቂነት ፈፃሚ ለመሆን ሁለት መታት ገደማ የፈጀ ውይይት ከዓለም ባንክ የስራ ሃላፊዎች ጋር መደረጉን ገልጸዋል፡፡ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በመንግስትና በህዝብ የተጣለበትን ሃላፊነት ለመወጣጥ ከፍተኛ የሪፎርም ስራዎች ውስጥ ማለፉን በማስታወስ በዚህም ግዚያት በርካታ ስራዎችን መስራታቸውን ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አክለው ገልጸዋል፡፡
በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችና ተቋማችንም እንዲሁም መንግስት መሃል ያለው ግንኙነት በትብብር ላይ የተመሰረተ መሆኑን በመግለፅ ባለስልጣኑ የጀመራቸውን የለውጥ ስራዎች ለማስቀጠል አጋር ድርጅቶች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ብለዋል ፡፡ የባለስልጣን መስርያቤቱ ዋና ዳይሬክተር በመጨረሻም ባስተላለፉት መልዕክት ቀደም ሲል ከዓለም ባንክ የተለያዩ ሃላፊዎችና ገንዘብ ሚኒስትር ሃላፊዎች ጋር በቀጣይ ስለምንሰራቸው ስራዎች ውይይት የተደረገ መሆኑን በማስታወስ ዛሬ የተጀመረው ስራ ቀጣይነት እንደሚኖረው ተስፋ እናደርጋለንም ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡