የቋሚ ኮሚቴ አባላቱ በተቋሙ የተመለከቱት ተግባር እጅግ አበረታች እና ደስተኛ መሆናቸውን በመግለጽ ዳግም ያልተመዘገቡ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን ጉዳይ ግን ትኩረት ተሰጥቶት ሊሰራ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ እንደገለጹት የተቋሙን አፈጻጸም በመመልከት ጠንካራ አፈጻጸሞችን ለማስቀል እና በአፈጻጸም ወቅት የታዩ ክፍተቶች ካሉም ለማመላከት በመገኘታቸው ምስጋቸውን አቅርበዋል፡: ስለተቋሙ ዋና ዋና አፈጻጸሞች ያጋጠሙ ችግሮች፣የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች እና የተከበረው ምክር ቤት ሊያውቋቸው የሚገቡ ጉዬችን በተመለከተ የተቋሙ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ ማብራሪያ አቅርበዋል፡፡
የተከበሩ አቶ ኢሳ ቦሩ የህግ ፍትህና ዲሞክራሲ ቋሚ ኮሚቴ ም/ሰብሳቢ ከምልከታው በኋላ በሰጡት አስተያየት የበጎ ግቃደኝነትና የበጎ አድራጊነት ስራን በማህበረሰቡ ዘንድ ባህል ለማድረግ የተከናወኑ ተግባራት፣በተቋሙ የሚሰጡ አገልግሎቶችን በኦላይን መጀመሩ፣በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳይ ላይ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችን የማስተባበር ስራ መሰራቱ፣የአገልግሎት አሰጣጥ መሻሻል ፣ከክልሎች ጋር የተጀመረው የጋራ ጉባኤ ፣የመማክርት ጉባኤ መመስረት እና ሌሎች በርካታ የተከናወኑ ተግባራት አበረታች መሆናቸውን በመግለጽ ዳግም ያልተመዘገቡ ድርጅቶችን መረጃ ማጣራትና ውሳኔ መስጠት፣መዝገብ ቤትን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ማስደገፍ እና ክልሎች የህግ ማዕቀፍ እንዲያዘጋጁ ድጋፍ ማድረግ ላይ ተቋሙ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ይገባዋል ሲሉ ገልጸዋል፡፡ በመጨረሻም የቋሚ ኮሚቴ አባላቱ በተቋሙ የተመለከቱት ስራ በጣም ጥሩ መሆኑን በመግለጽ ለቋሚ ኮሚቴ አባላቱ እንዲመለከተው ያነሳችሁትን ጉዳይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ለመፍታት እንሰራለን ብለዋል፡፡