ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የ2014 በጀት ዓመት የስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸሙን ከባለድርሻ አካላት ጋር እየገመገመ ይገኛል፡፡
በመድረኩ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የፍትህ ሚንስቴር ሚኒስትር ደኤታ አለምአንተ አግደው እንደገለጹት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በሃገራችን የልማት እንቅስቃሴ እና የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ የማይተካ ሚና እንዳላቸው በመንግስት በኩል ጽኑ እምነት አለ ያሉ ሲሆን የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በታሪክ የተፈጠረላቸውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም በሃገራዊ ጉዳዬች ላይ በተለይም የህግ የበላይነት በማረጋገጥ፣ሰላምን በማስፈንና ግጭቶችን በመፍታት ሂደት ትርጉም ባለው መልኩ አዎንታዊ ሚና መጫወት ይኖርባቸዋል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ከግዜ ወደ ግዜ የተሻለ አቅም እየገነቡ እና መልካም አስተዋጽኦ እያደረጉ መሆኑን በሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎች መገንዘብ ይቻላል፡፡ በሃገራዊ ጉዳይ ሲማዶች በጦርነትና በድርቅ ለተጎዱ አከባቢዎችና የህብረተሰብ ክፍሎች በገንዘብና በዓይነት እያደረጉ ያሉት ድጋፍ አንድ ለህዝብ ተጠቃሚነት ከቆመ ዘርፍ የሚጠበቅ በመሆኑ ምስጋና የሚገባው መሆኑን በመጠቆም ሲማዶች በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳይም ሆነ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ በማድረግ ረገድ እያደረጓቸው ያሉት አስተዋጽኦዎች መንግስት ከፈጠረው ምቹ ሁኔታ እና ከሃገርና ህዝብ ፍላጎት አንጻር አሁንም ብዙ የሚቀረው ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡ በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዘርፉ ህግና ስርዓትን ተከትሎ ውጤታማ ስራ እንዲያከናውን የጀመረውን የክትትል፣የድጋፍ፣የአሳታፊነት እና ቅንጅታዊ ስራ አጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል ሲሉ የተቋሙ አመራሮችና ሰራተኞች ላስመዘገቡት መልካም ውጤት አመስግነዋል፡፡
የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ በበኩላቸው በሀገሪቱ ላይ የመጣውን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ ከጸጥታ ኃይላችን ጎን ለጎን በጦርነቱ ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ በማቋቋም ሂደት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች አይተኬ ሚና የተጫወቱ መሆኑን አንስተው ባለስልጣን መስሪያቤቱ ያቀረበላቸውን አገራዊ ጥሪ ተቀብለው ከ350 ሚሊየን ብር በላይ የዓይነትና የገንዘብ ድጋፍ በማሰባሰብ በጦርነቱ ለተጎዱ ዜጎች ማድረስ መቻሉን ገልፀዋል፡፡ አያይዘውም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከጊዜ ወደጊዜ የአሰራር ስዓቱን በማዘመን ከ45 በላይ አገልግሎቶችን በኤሌክትሮኒክ ሰርቪስ በመስጠት ላይ ይገኛል ሲሉ በመግለጽ የተቋሙን የመፈጸምና የማስፈጸም አቅም ለማጎልበት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ሰፊ የምክክር መድረኮችን በማድረግ ወጥነት ያለው የአሰራር ስርዓት ለማጎልበት ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡
ሌላው ዋና ዳይሬክተሩ ያሱት ለዘመናት ስንናፍቀው የነበረው ታላቁ ህዳሴ ግድብ እውን ሆኖ የመጀመሪያ ምዕራፍ ተጠናቆ ኃይል ማመንጨት በጀመረበት ማግስት መሆኑና የዚህ ድል ባለቤት በመሆናችን እኳን ድስ ያለን ብለዋ፡፡ ከሪፖርቱ በተጨማሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን እና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከባለስልጣን መስሪያቤቱ ጋር በቀጣይ አብሮ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት የተፈራረሙ ሲሆን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በዛሬው እለት የኢ-ሰርቪስ አገልግሎትን በይፋ ያስጀምራል፡፡