ተቋሙ ከጀስቲስ ፎር ኦል ጋር በመተባበር በሁለት ዙር ያዘጋጀው ስልጠና ሲሆን በኢፕሳስ (IPSAS) ግንዛቤ እና አተገባበር ዙሪያ ትኩረት እንደሚያደር ተገልጿል፡: በስልጠናው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሲቪል ማህበረሰብ ደርጅቶች ባለስልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ ባስተላለፉት መልዕክት ቀደም ሲል ተቋማችን በርካታ የሪፎርም ስራዎችን እየሰራ እንደነበር በማስታወስ በተለይም የባለሙያውን አቅምና ክህሎት ማሳደግ ትኩረት ከተሰጡት ውስጥ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ለተቋሙ የተሰጠውን ተግባርና ሃላፊነት በአግባቡ ለመወጣትና ውጤታማ ስራ ለማከናወን ጥረት እያደረገ መሆኑን በመናገር ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ የተለያዩ ስልጠናዎችን በመስጠት አቅም ግንባታ ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
ለውጡ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ የተሻለ ለውጥ በተቋሙ እየተመዘገበ ነው ያሉት ም/ዋና ዳይሬክተሩ የተሻለ የመፈፀምና የማስፈፀም አቅም ያላቸው ባለሞያዎችንም እያፈራን እንገኛለን ብለዋል፡፡ አያይዘውም በቀጣይ ተጨማሪ ሙሉ አቅም ያላቸው በርካታ ባለሙያዎችን ማፍራት ይጠበቅብናል ለዚህም ሲባል ነው ቴክኖሎጂን ያማከሉ አለም አቀፍ አሰራርን መሰረት ያደረጉ ስልጠናዎችን እንድትወሰዱ የተደረገው ሲሉ ለሰልጣኞች መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ የጀስቲስ ፎር ኦል መስራችና ዳይሬክተር እንዲሁም የኢትዮጵያ የሃገር ሽማግሌዎች መማክርት አባል የሆኑት ፓስተር ዳንኤል ገ/ስላሴ በሰላም ዙርያ ያዘጋጁትን ዶክመንተሪ ፊልም ማብራርያ እየሰጡ በሃገር ሰላም ዙርያ ልምዳቸውን ለሰልጣኞች አካፍለዋል፡፡

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በዋናነት ከተሰጡት ተግባርና ሃላፊነቶች መካከል ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር በተያያዘ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ ሲሆን ይህም በፋይናንስ አመራር ላይ የተዘጋጀው ሰልጠና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የሚያቀርቡትን ሪፖርቶችን በአግባቡ መገምገም እንዲቻል እንዲሁም ተገቢውን ግብረመልስ ለመስጠት ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ከመረጃዎችም ለመረዳት እንደቻልነው ይህ የኢፕሳስ(IPSAS) አሰራር130 በላይ ሃገራት እንደሚጠቀሙበት ተመላክቷል፡፡