በጉብኝቱ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር እና ም/ዋና ዳይሬክተርን ጨምሮ የተለያዩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ተወካዬች ተገኝተዋል፡፡ ፕሮግራሙ የተዘጋጀው የበጎ ፍቃድ ቀን ሲከበር ከንግግር በዘለለ በተግባር ሆኖ ለማሳየት መሆኑ ተገልጷል፡፡
ስለእናት የበጎ አድራጎት ድርጅት ‹‹የተሻለ የልጅነት ጊዜ ለሁሉም ህጻናት›› የሚል መሪ ቃል ያለሁ እና ህጻና ላይ በተለይም የአካል ጉዳት ያለባቸው ህጻናት ላይ የሚሰራ ሃገር በቀል ድርጅት ነው፡፡ ድርጅቱ ከተመሰረተ 20 ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን በዚህ የአገልግሎት ቆይታ ብዙ ስኬቶችን እና ውጣ ውረዶችንም ማሳለፉን ከገለጻ ለመረዳ ተችሏል፡፡
ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ እንደገለጹት በዓለም ዓቀፍ የበጎ ፍቃደኞች ቀን ሲከበር ድርጅቱን በመጎብኘታቸው ደስተኛ መሆናቸውን በመግለጽ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ዘርፍ ለሃገር ልማት፣ዴሞክራሲ፣ሰላም እና መንግስት የማይሸፍናቸውን ዘርፎች ተደራሽ የሚያደርግ ዘርፍ መሆኑን አብራርተዋል፡: ከኩሶ ኢንተርናሽናል ድርጅት ጋር በጋራ በመሆን ለድርጅቱ የሚሆኑ የተለያዩ ቁሳቁሶችን ስናመጣ ፍቅራችንን ለመግለጽ እንጂ ለድርጅቱ የተለየ ለውጥ ያመጣል በሚል ያለመሆኑን አብራርተዋል፡፡ አያይዘውም ሃገር የምትቀጥለው በበጎ ፍቃደኞች ነው፡፡ ዛሬ የህይወት መስዋትነት እየከፈሉ ያሉት በበጎ ፍቃደኝነት እና ሃገር ወዳድነት ነው፡፡ ስለሆነም ኢትዬጵያ እንደ ሃገር ጥሪ እያደረገች ባለችበት በዚህ ወቅት ሁሉም አካል የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡