ይህ የተገለፀው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ ከሜሪ-ጆይ ልማት ማህበር በጎ ፈቃደኛ የኪነጥብብ ባለሙያዎች ጋር በካፒታል ሆቴል በቀን12/09/2013 ዓ.ም የውይይት መድረክ ላይ ነው፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሲቪል ማህበረሰብ ደርጅቶች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ እንደገለፁት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ 1113/2011 መሰረት በህገ መንግሰቱ የተረጋገጠውን የመደራጀት መብት በተሟላ ሁኔታ  በማክበር የሲቪል ማበረሰብ ድርጅቶች ህግን አክብረው እንዲንቀሳቀሱ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ በሀገራችን የበጎ አድራጊነትና በጎ ፈቀደኝነት  ባህልን በማጎልበትና በማስረጽ ድርጅቶት በሀገር ልማትና ደሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ላይ ጉልህ አስተዋጽኦ እንዲኖራቸው በማስቻል፣ የነቃና የተደራጀ ማህበረሰብ በመፍጠር፣ የህብረተሰቡን የላቀ ተጠቃሚነትና የሀገራችንን ሁለንተናዊ ብልጽግና ማረጋገጥ በሚል ተልዕኮ በአዲስ መልክ ተዋቀሮ ተልኮውን በአግባቡ ለመወጣት ከባለደረሻ አካላት ጋር በትብብር እየሰራ እንደሚኝ ገልፀዋል፡፡

አያይዘውም ኤንሲው በአዋጅ የተሰጠውን “የበጎ አድራጎትና የበጎ ፈቃደኝነት ባህል በህብረተቡ  ዘንድ ማሳደግ” ተግባረና ሀላፊነት በተሟላ ሁኔታ ለመፈጸም እና ዘርፉን ለመምራት የሚያስችለው ተቋማዊ አደረጃጀት የፈጠረ ሲሆን ከኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ጋር ቅንጅታዊ  አሰራር በመፍጠር ዘርፉ ለሀገር ልማትና ለህብረተሰቡ ተጠቃሚነት የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ ለማሳደግ እንደሚያስችል ተናግረዋል፡፡

የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች የበጎ አድራጎትና የበጎ ፈቃደኝነት ባህል ከማጎልበት አኳያ ከፍተኛ ሚና አንዳላቸው የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥም የበጎ አድራጎትና የበጎ ፈቃደኝነት ባህል ከማስፋፋትና ከማስረጽ አኳያ በራሳው ተነሳሽነት በስነ ጽሁፍ በቲያትር በሰነ ስዕል፣ በድራማ በፊልማ እና በተለያዩ መንገዶች እንዲሁም በልማት በኢኮኖሚ፣ በሰብዕና ግንባታ፣ በትምህርት፣ በጤና እና በማህበራዊ ጉዳዮች ማህበረሰቡን በማንቃት ከፍተኛ አሰተዋጽኦ እያበረከቱ መሆን አንስተዋል፡፡