የሒሳብ አጣሪ የጨረታ ማስታወቂያ

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በተሸሻለው በአዋጅ ቁጥር 1113/2011 ለባለሥልጣኑ በርካታ ኃላፊነት አዋጁ የሰጠው መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከነዚህ ኃላፊነቶች ውስጥ አንዱ ድርጅት ሲፈርስ የፈረሰውን ድርጅት ሀብት እና ዕዳ የሚያጣራ የሂሣብ አጣሪዎች ሹመት በመስጠት የድርጅቱን ሀብት ለሕዝብ ጥቅም እንዲውል ማድረግ ነው፡፡

በመሆኑም ባለሥልጣኑበአዋጅ ቁጥር 1113/2011 እና በመመሪያ ቁጥር 850/2014 አንቀፅ 5 መሰረት የሂሳብ አጣሪ መዝገብ (ሮስተር) ማዘጋጀትአስፈላጊ ስለሆነ ከታች የተቀመጡትን መስፈርት የምታሟሉ ይህ ማስተታወቂያ ከወጣ ቀን ጀምሮ ባሉ ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅች ባለሥልጣን ፈንድ አስተዳደር እና ንብረት ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ቢሮ ቁጥር 608 ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ አስከ ዓርብ ከጧቱ 2፡30 እስከ 11፡00) በአካል በመቅረብ ያላችሁን የትምህርት ማስረጃ ፣ የሥራ ልምድ እና ሌሎች አስፈላጊ ሰነዶች መመዝገብ የምትች

ሉ መሆኑን እንገልጻለለን፡፡

ለሂሣብ አጣሪነት ለመመረጥ የሚያበቁ መመዘኛዎች

ለሂሣብ አጣሪነት ለመመረጥ የሚያበቁ መመዘኛዎች የሚከተሉት ናቸው፤

 

  • የተፈጥሮ ሰው የሆነ፤
  • በሂሳብ አጣሪነት አግባብ ካለው አካል የተሰጠ የሙያ ማረጋገጫ ያለው ወይም በሕግ፣ በሂሣብ ወይም በማኔጅመት ሙያ ወይም ተያያዥነት ባለው የሙያ መስክ የሰለጠነ እና ቢያንስ 2 ዓመት የሂሣብ አጣሪነት ልምድ ያለው፤
  • የኢትዮጵያ ዜጋ ወይም ኢትዮጵያ ውስጥ ቋሚ ወይም መደበኛ ነዋሪ የሆነ፤
  • ከሂሣብ ማጣራትና ተዛማጅ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ በወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ ያልተገኘ፤
  • በሙስና፣ በምዝበራ፣ በማጭበርበር ወይም በእምነት ማጉደልና ማታለለል ወንጀል ጥፋተኛ    ሆኖ ያልተገኘ፤
  • በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) (መ) እና (ሠ) በተመለከቱት ወንጀሎች ተከስሶ ጉዳዩ በፍርድ ቤት ላይ በመታየት ላይ ያልሆነ፤
  • ላለፉት 24 ወራት የሚፈርሰው ድርጅት ኦዲተር ወይም የሂሳብ ባለሙያ ወይም በድርጅቱ የአመራር አባል የሆነ ሰራተኛ ወይም ከሂሳብ ማጣራቱ ስራ ጋር ቀጥታ ግንኙነት የሌለው ማንኛውም ሰው፡፡

ምዝገባው የሚካሄደ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ፈንድ አስተዳደርና ንብረት ጉዳዮች መሪ ስራስፈጻሚ ቢሮ ቁጥር 608 ዘወትር በስራ ስዓት ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን

 

Privacy Preference Center

Skip to content