ለሶስት ቀናት በሚቆየው በዚህ ስልጠና በስነ ምግባርና አገልጋይነት፣ በሙስና ጽንሰ ሀሳቦችና ዓይነቶች እንዲሁም በሙስና መከላከል መንገዶች ላይ የሚያተኩሩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በመጀመሪያው ክፍል የሚሰጥ ሲሆን በመንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010 እንዲሁም የሰው ኃብት እቅድና ስምሪት፣ የስራ አፈጻጸምና የደረጃ እድገት፣ የስራ ሰዓትና ፈቃድ እንዲሁም የዲሲፒሊን ርምጃዎችን ጨምሮ መብትና ግዴታዎችን የተመለከቱ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በቀጣዮቹ ቀናት ስልጠናው የሚሰጥ ይሆናል፡፡

በስልጠናው መክፈቻ ላይ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የሰው ኃብት ልማትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደጀኔ ጌታቸው እንዳሉት ይህ ስልጠና መሰረታዊ በመሆኑ በስራ ሂወታችሁ ብቻ ሳይሆን በየትኛውም ተቋም ጠቃሚ ነው ብለዋል፡፡ አያይዘውም የተቋሙ ሰራኞች ብቁና ውጤታማ እንዲሆኑ በቀጣይም የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ከመስጠት ረገድ ትኩረት ተሰጥቶት ይሰራል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የስነ ምግባር መከታተያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት አቡዬ በበኩላቸው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በአዋጅ የተሰጠውን ስልጣንና ተግባር ለማስፈጸም በሚያደርገው ሂደት ውስጥ የተቋሙ ሰራተኞችና አመራሮች ከሙስና በጸዳና ስነምግባርን በተላበሰ መልኩ ሊሰሩ ይገባል ሲሉ ገልጸዋል፡፡ ስልጠናው ዛሬን ጨምሮ ለቀጣዮቹ ሶስት ቀናት የሚቀጥል ሲሆን ከስልጠናው በኋላ በስራ አካባቢያቸው መብትና ግዴታቸውን አውቀው መልካም ስነምግባርን ተላብሰው ለተቋሙ ውጤታማነት ቀደም ሲል ያደርጉ ከነበረው በተሻለ መልኩ እንደሚያበረክቱ ይጠበቃል፡፡