የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬተርን ጨምሮ የኤጀንሲው ከፍትኛ የስራ  ኃላፊዎች አበበች ጎበና የህፃናት እንክብካ ልማት ማህበርን ጎብኝተዋል፡፡ የማህበሩን የስራ እንቅስቃሴ የተመለከቱት የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ እንደገለጹት የኤጀንሲው ስኬት የሚለካው የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በሚያስመዘግቡት ውጤት በመሆኑ ይበልጥ ውጤታማ እንድትሆኑ በማገዝ ረገድ ሁሌም ከጎናችሁ ነን ሲሉ በጉብኝቱ ወቅት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም ማህበሩ ራሱን በፋይናንስ ለመደገፍ እያደረገ ያለው ጥረት እጅግ የሚበረታታና ይበልጥ ሊጠናከር የሚገባው መሆኑን አንስተው ከመንግስትና ከሌሎች የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጋር የስትራቴጂክ አጋርነት መፍጠር፤ አዳዲስ ሀሳቦችንና አሰራሮችን መሞከር፣ አበበች ጎበና የሚለው ስም ትልቅ ብራድ በመሆኑ ማህበሩ ሊጠቀምበትና በጎ አድራጊዎችን ሊስብበት እንደሚገባ አንስተዋል፡፡ ማህበሩ ላለፉት 42 ዓመታት ሲሰራ መቆየቱ እጅግ ትልቅ ስኬት መሆኑን አንስተው የክብር ዶክተር አበበች ጎበና ታሪክ ለበርካታ ሰዎች ምሳሌ የሚሆን በመሆኑ በዚህ እረገድ በርካቶችን መፍጠር ስለምንፈልግ ድጋፋችን ከእናንተ ጋር ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
አቶ እሸቱ አረዶ የህጻናት ልማት ማህበሩ ማኔጂንግ ዳይሬክተር በበኩላቸው የልማት ማህበሩ ላለፉት ረጅም አመታት እጅግ በርካታ ስራዎችን ሲሰራ የቆየ ቢሆንም አሁን ላይ ድርጅቱ ችግሮች እያጋጠሙት ስለሆነ ትኩረት ሰጠቶ ሊደግፍው ይገባል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ስለ ድርጅቱ ማብራሪያ የሰጡት የድርጅቱ የኮሙኒኬሽን ሃላፊ እንዳነሱት ድርጅቱ ከተመሰረተ 42 ዓመታትን ክማስቆጠሩም ብላይ ወላጅ አልባ ህፃናትን ብቻ ሳይሆን ከህጻናት ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ስራዎችን ማልትም የህፃናት እንክብካቤ፣ የወጣቶች ስልጠና፣ የባልትናና የዕደ ጥበባት ስራዎች፣ የጤና አገልግሎት፣ የሴቶች አቅም ግንባታ ስልጠናዎችን እንዲሁም የአካባቢ ጥበቃዎችን እንደሚሰራ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡  የአበበች ጎበና የህፃናት ልማት ማህበር ሁለት ህፃናትን በማንሳት ከ42 ዓመት በፊት በክብር ዶክተር አበበች ጎበና የተመሠረተ ማህበር ሲሆን በአሁን ጊዜ ከ300 ሺህ በላይ ዜጎችን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ እያገዘ ያለ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ነው፡፡