ግልጽ የፕሮፖዛል መቀበያ ጥሪ

ግልጽ የፕሮፖዛል መቀበያ ጥሪ ማስታወቂያ

በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ  ቁጥር 1113/2011 አንቀፅ 86 መሰረት በሲቪል ማህበረሰብ  ድርጅቶች  ባለሥልጣን  የሚተዳደር  የሲቪል ማህበረሰብ  ፈንድ እንደሚቋቋሙም ተደንግጓል ፡ ባለስልጣን መስርያ ቤቱ ይህንኑ በሚመለከት  ባወጣው የሲቪል ማህበረሰብ ፈንድ አስተዳደር  መመርያ  ቁጥር  848/2014 መሰረት በፈንዱ ተጠቃሚ  የሚሆኑት  በባለስልጣኑ  ተመዝጋቢ አገር በቀል  የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች  ብቻ ሲሆኑ  የፈንዱም አላማ  በጎ ፈቃደኝነት እና  የዘርፉን እድገት ማበረታታት ፡ የሲቪል ማህበረሰብ ድረጅቶችን አገራዊ አስተዋተዋጽዖ ማበረታታት እና  ልዩ ድጋፍ  የሚያስፈልጋቸው  የህብረተሰብ  ክፍሎች  ዙርያ  የሚሰሩ  ድርጅቶችን ማበረታታትና ማገዝ   ነው፡፡

በመሆኑም ባለስልጣን  መስረያ ቤታችን  ከፈንዱ ድጋፍ ለማድረግ አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎችን  ያጠናቀቀ ሲሆን በ2015 ዓ.ም ከፈንዱ የድጋፍ  ትኩረት  ነጥቦች ሃገራችን  ኢትዮጵያ  አሁን ካለችበት  ወቅታዊ  ሁኔታ አንፃር በጦርነት ምክንያት  ከቤት ንብረታቸው  የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም የሰብዓዊ እና የማህበራዊ ሥነ-ልቦና /psychosocial/ ድጋፍ ላይ ለመስራት ፈቃደኛ ለሆኑ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የፋይናስ ድጋፍ ማድረግ ነው ፡፡በዚህም መሰረት በተጠቀሱት የትኩረት ነጥቦች ላይ አሳማኝ እና ችግር ፈች የሆኑ ፕሮጀክት ፕሮፖዛሎችን ለሚያቀርቡ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የፋይናንስ ድጋፍ ለማድረግ ይህንን ግልጽ የፕሮፖዛል መቀበያ ጥሪ ማስታወቂያ አውጥቷል፡፡

ስለሆነም ለዚህ ግልጽ የፕሮፖዛል መቀበያ ጥሪ ማንኛውም አገር በቀል ድርጅት ከፈንዱ የፋይናንስ ድጋፍ ለማግኘት የሚያቀርባቸው ሰነዶች የሚከተሉት ዝርዝሮችን የያዘ መሆን ይኖርበታል፡፡

ሀ. የድርጅቱን ዝርዝር እቅድ የሚያሳይ የቴክኒክ እና የፋይናንስ ጉዳዮችን ያካተተ

ፕሮጀክት ፕሮፖዛል

ለ. አስቀድሞ የተቋቋመና ከሌሎች ለጋሾች ገንዘብ ያላገኘ ድርጅት መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰነድ

ሐ. ማመልከቻውን ከሚያቀርበብበት አመት በፊት የተዘጋጀ አመታዊ የክንውን እና የፋይናንስ    ሪፖርት

መ. በአንድ ድርጅት መቅረብ የሚችለው ፕሮጅክት ፕሮፖዛል አንድ ብቻ ሲሆን አነስተኛ የፕሮጅክት መተግበሪያ  ጊዜ ስድስት ወር  /ግማሽ አመት/ መሆኑን  በግልጽ በሚያሳይ መልኩ  ማስቀመጥ  አለበት።

ሠ. ባለስልጣን መ/ቤቱ ለአንድ ፕሮጀክት ፕሮፖዛል  ከፈንዱ ድጋፍ  የሚያደርገው  የገንዘብ ጣሪያ እስከ ብር 3,000,000.00/ሦስት ሚሊዮን ብር /በመሆኑ የሚቀርበው ፕሮጀክት ፕሮፖዛል አስተዳደራዊ እና አላማ  ማስፈጸሚያ ወጭ ከተጠቀሰው  የገንዘብ መጠን  መብለጥ የለበትም ፡፡

ረ. የሚቀርበው ፕሮጀክት ፕሮፖዛል ይዘት ርዕስ  ማውጫ  መግቢያ ግብ ዝርዝር አላማወች የማስፈጸሚያ ስልቶች የሚጠበቀው ውጤቶች  የተግበራት ዝርዝር የክትትልና ድጋፍ ስርዓት የማብቂያ /የማስረከቢያ ስትራቴጂ ያካተተና ከ15 ገጽ ያልበለጠ መሆኑአለበት፡፡

ተወደዳሪዎች ይህ ግልጽ የፕሮፖዛል መቀበያ ጥሪ ማስታወቂያ በአዲስ  ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን  ጀምሮ ባሉት አስር  /10/ተከታታይ የስራ ቀናት  ውስጥ ከላይ የተዘረዘሩትን የመወዳደርያ  ሰነዶች በማሟላት  አዲስ አበባ ከተማ ቴዎድሮስ አደባባይ ከፍ ብሎ ሕብረት ኢንሹራንስ ህንጻ 6ተኛ  ፎቅ ከሲ/ማ/ድ/ፈንድ/አስ/ እና ን/ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈፃሚ ቢሮ ቁጥር 608 ማስረከብ አለባቸው ፡፡ በአስረኛው የስራ ቀን  የመወዳደርያ ሰነድ የሚገባው እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ ብቻ  መሆኑን እናስታውቃለን ፡፡

ማሳሰቢያ

በባለስልጣን ድጋፍ ለማድረግ የተሻለ መንገድ ካገኘ ማስታወቂያውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ እንደተጠበቀ ነው፡፡

በተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ በቁጥር 0911999628፣0918156115፣0910204768 እና 0115522437 በስራ ሰአት ብቻ ይደውሉ፡፡

            

           የኢትዮጵያ ፌዴራልዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን

 

የፕሮጀክት ፕሮፖዛል ቅጽ

 • የፕሮጀክቱ ርዕስ /Project Title)
 1. Executive Summary
 2. መግቢያ /Introduction/
  • ስለድርጅቱ አመሰራረት /Background of the Organization/
  • Main Achievements of the Organization
  • Project Area
 3. የችግሩ ዳራ /Problem Statement/
 1. Project Description
  • Project Descriptions
  • አላማ /Goals/
 • አላማዎች / Objectives/
 1. የፕሮጀክት መፈጸሚያ ስልት /Strategy/
 2. ከፕሮጀክቱ የሚጠበቅ ውጤት /Expected Results/
 3. ተግባራት (Activities)
 4. የክትትልና ግምገማ ስርአት /Monitoring & Evaluation/
 1. የፕሪጀክቱ ቀጣይነት (የመውጫ ስልት) /Sustainability/Exit Strategy/

በጀት /Budget break down per objective/

Privacy Preference Center

Skip to content