የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ አመራሮችና ለሚመለከታቸው ስራክፍሎች ባለሙያዎች አሰራሩን የኦን ላይን አገልሎት ለመስጠት የሚስችለውን የኢ-ሰርቪስ አገልግሎት አሰጣጥ ዙርያ በቢሾፍቱ ከተማ አዱላላ ሪዞርትለሁለት ቀናት የቆየ  ስልጠና ተሰጠ፡፡

ኤጀንሲው የህብረተሰቡን የላቀ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ቀደም ሲል የነበረውን አዋጅ 621/2001 ሙሉ በሙሉ በ1113/2011 ከቀየረ በኋላ በውስጥ አሰራሩና የባለሙያውን አቅም ከመገንባት አንጻር የተለያዩ ስልጠናዎችን በመስጠት በርካታ የሪፎርም ስራዎችን በመስራት መልካም የሚባሉ ውጤቶችን ማምጣት መቻሉ የሚታወስ ነው፡፡

ከዚህም ባሻገር ተቋሙ በቀጣይ ምዕራፉ መንግስት ባስቀመጠው የኢ-ሰርቪስ አገልግሎት በኦን ላይን ለመጀመር የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆኑን የሚያመላክቱ እንቅስቃሴዎች እያደረገ ይገኛል ለዚህም ግብዓት ሚሆኑ ቅድመ ዝግጅቶች እያደረገ ነው፡፡

የኮሙኒኬሽንና ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ትግስት ዳኝነት የኢ-ሰርቪስ አገልግሎት ለማስተጀመር እንዲሁም ቀጥታ የኦን ላይን አገልግሎት ለመስጠት ኤጀንሲው ዝግጅት እያደረገ መቆየቱን በማስታወስ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በኤጀንሲው በዋናነት በኦንላይን አገልግሎት መስጠት በሚቻልባቸው የስራ ክፍሎች እና አገልግሎት መስጠት ያስችላል በተባሉት አርባ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ በመለየት ስልጠናውን ማዘጋጀት ተችሏል ብለዋል ፡፡

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ ስልጠናውን በተመለከተ በኮሙኒኬሽንና ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት በኩል ባስተላለፉት መልዕክት የኢ-ሰርቪስ አገልግሎት በተቋማችን ቅድሚያ የሚሰጠው እንደመሆኑ መጠን ተገቢውን ትኩረት በመስጠት ከባሙያዎቹ የሚሰጡትን ስልጠናዎች መከታተል ይኖርባችዋል፤ ይህም በቀጣይ የኦንላይን አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅታችንን በማጠናቀቅ ወደትግበራ ለመግባት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንሚያበረክትም በማመላከት በድጋሚ በስልጠናው ላይ በመሳተፍ የተገኛችሁ ሰልጣኞች ተገቢውን ትኩረት በመስጠት መከታተል ይኖርባችዋል በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የምክትል ዋና ዳይሬክተር አማካሪ አቶ ሃይለስላሴ ገ/ሚካኤል እንዳሉት ኤጀንሲው በርካታ የሪፎርም ስራዎችን በመስራት ውስጥ ማለፉን በመግለጽ በዚህም በአቅም ግንባታው ላይ እና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ  በርካታ ስራዎች እንደተሰሩና ውጤትም እንደተገኘባቸው ተናግረዋል፡፡

ይህም ዛሬ በጋራ የምንሰለጥነው የኢሰርቪስ አገልግሎት አሰጣጥ አሰራራቸውን በኦን ላይን እንዲተገብሩ ከተደረጉት ሃያ የሚሆኑ የመንግስት ተቋማት ውስጥ የኛ ተቋም ከሚሰጠው አገልግሎት አንፃር አንደኛው ተቋም ተደርጎ ተመርጧል ይህም የአገልግሎት ፈላጊውን ድካም የሚቀንስልን መሆኑንና አሰራራችንን በማዘመን የተገልጋዮቻችን የተሻለና የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት ያስችለናል ብለዋል፡፡

በመጨረሻም በ2014 ዓ.ም በጀት ዓመት ከተቀመጡት የትኩረት አቅጣጫዎች ውስጥ የኢ-ሰርቪስ አገልግሎት በተቋማችን ማስጀመር እንደመሆኑ መጠን ይህንን ተግባር ላይ ለማዋል ኮሚቴዎችን በማዋቀር በአገልግሎቱ ዙርያ ስልጠና መሰጠን አሰታውሰዋል፡፡

በመጨረሻም የዋና ዳይሬክተሩ አማካሪ አቶ ተስፋዬ ሽፈራው ባስተላለፉት መልዕክት የኢ-ርቪስ  አገልግሎት የተገልጋዩን እርካታ ከፍ እንደሚያደርገው እና በተገኘው ስልጠና ግንዛቤ የተጨበጠበት መሆኑን ያመላክታል ይህም ትልቁ ግባችን ሲሆን ተግባራዊ የሚሆነውም አገልግሎቱን በአግባቡ ተረድትን ስራ ላይ ስናውለው ነው ብለዋል፡፡

የመደራጀት መብት፤ ሰብዓዊነት፤ የኅብረተሰብ የላቀ ተጠቃሚነት!!