በውይይት መድረኩ የመክፈቻ ንግግር  ያደረጉት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ እንደገለጹት አሁን ሀገራችን  ኢትዮጵያ እጅግ  ፈታኝ በሆነ  ወቅት ላይ እንደምትገኝ ገልጸው በተለይም ፅንፈኛው የህወሓት ጁንታ ቡድን በሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ  የፈፀመው  ጭካኔ ሳያንሰው ከውጭ ወራሪ ኃይሎች ጋር በማበር ኢትዮጵያን የመበታተንና የማፍረስ አጀንዳ ዓላማዬ ብሎ በመያዝና በሀገርቱ ላይ ጦርነት በማወጅ፣የሀሰት ፕሮፓጋንዳና ውዥንብር በማሰራጨት በሀገራችን የተጀመረው ለውጥ እንዲጨናገፍና የሀገራችን የብልፅግና ጉዞ እንዳይሳካ ለማድረግ እንዲሁም የኢትዮጵያ አንድነትና ወንድማማችነት ላይ ችግር ሲፈጥር መቆየቱን ገልጸዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩም አክለውም ኢትዮጵያን በብሔር፣ በጎሣና  በሃይማኖት በመከፋፈል ኢትዮጵያ ከክብሯ ዝቅ ብላ እንድትታይ ከማድረጉም በላይ በሀገሪቱ የዜጎች ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብት  እንዳይከበር፤ ዜጎች በሠላም ወጥተው እንዳይገቡ፣ ከመኖሪያ አካባቢያቸው እንዲፈናቀሉ፣ንፁሃን ዜጎች በግፍ እንዲገደሉ በማድረግ  ሀገርን የማፍረስ አጀንዳ ከውስጥና ከውጪ ጠላቶቻችን ጋር በመቀናጀትና ተላላኪ በመሆን  በሀገራችን ላይ የሞት ሽረት ጦርነት የከፈተ ቢሆንም  ሀገር ወዳድ እና የቁርጥ ቀን ልጆቿ ከዳር እስከዳር በአንድነት በመነሳት  ይህንን ከሃድ ቡድን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ  ለማስወገድ በአንድነት ተነስተው በግንባር በመፋለም ላይ እንደሚገኙ ገልጸው ሁላችንም ይህንን በሀገራችን  ላይ የተከፈተብን ወረራ ለመመከት በገንዘብ፣ በቁሳቁስ፣ በሞራል እና አልፎም በአካል በግንባር ድረስ በመሄድ ከጀግናው መከላከያችን ጎን መሆናችንን በተግባር ማረጋገጥ ይጠበቅብናል በማት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል

በመጨረሻም በበጀት ዓመቱ በተቋሙ በርካታ ስራዎች እንደተከናወኑ አብራርተው 2014 በጀት ዓመት  ከባለፈው ዓመት በተሻለ  የአገልግሎት አሰጣጣችንን ወደ E-SERVICE  በመቀየር ተደራሽና ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት እንዲሁም 781 አዳዲስ አገር በቀል እና የውጭ ድርጅቶችን ለመመዝገብ እና ሌሎች እቅዶች የተያዙ ሲሆን የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የማያረጋግጥ የሲቪል ማኅበረሰብ ዘርፍ ለመፍጠር እና የሲቪክ ባህሉ የጎለበተ፣የነቃና የተደራጀ ማኅበረሰብ የመፍጠር ሪዕያችንን ለማሳካት ተቋማችን ከመቼውም በላይ በከፍተኛ ትጋት ይሰራል ብለዋ፡፡

የ2013 እቅድ አፈጻጸም እና የ2014 እቅድን የኤጀንሲው እቅድ፣በጀትና ለውጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ቃልኪዳን መንግስቴ አቅርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በኤጀንሲው አዲስ የተገነባው ድረገጽን የማስተዋወቅ ስራ ተሰርቷል፡፡