በሲ.ማ.ድ ፈንድ አስተዳደርና ንብረት ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ የሚሰጡ አገልግሎቶች
የሲ.ማ.ድ ፈንድ አስተዳደርና ንብረት ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ
- መመሪያዎችንና አሰራሮችን በየጊዜው እንዲፈተሹና እንዲሻሻሉ ሀሳብ/ግብዓት ያቀርባል በወቅቱ እንዲፈቱ ያደርጋል፤
- በአፈጻጸም ሂደት የተገኙ ተሞክሮዎችን በመቀመር ወይም እንዲቀመር በማድረግ የማስፋት ሥራን ይሰራል፤
- ከስራው ጋር ተያያዥነት ያላቸውን አጠቃላይ መረጃዎች ይሰበስባል፣ ይይዛል እና ለሚመለከታቸው ካላት ያስተላልፋል፤
- የሚዘጉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን ንብረት የማጣራት ስራዎችን ይፈጽማል፤ ይከታተላል፣
- ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የሚቀርቡ የንብረት ይወገድልን ወይም ይተላለፍልን ጥያቄ ከቀረበ በጥያቄው መሰረት ንብረት ይቆጥራል፤ ሰነዶችን ይመረምራል፤ ንብረቶቹ በአግባቡ ያደራጃል፤
- የተዘጉ ድርጅቶችን ንብረት በሚጣራበት ወቅት ወጪዎቹ በትክክል ኦዲት ስለመደረጉ ጥርጣሬ የሚያሳድር ሆኖ ከተገኘ በኤጀንሲው ኦዲተር ተሹሞ እንዲመረመር የውሳኔ ሃሳብ ያቀርባል፤
- የተመዘበሩና ከአላማቸው ውጪ የተጠቀሙበት ሀብት መኖሩን ከተረጋገጠም መረጃዎችን ያደራጃል፣የተዘጉ ድርጅቶችን ንብረት እዳና እገዳ ያለመኖራቸውን በጋዜጣ እንዲወጣና እንዲረጋገጥ ያደርጋል፣
- በሚዘጉ የድርጅቶች አመራሮች ሲሰሩበት የነበረውን የህዝብ ንብረት በአግባቡ አስረክበው ማጠናቀቃቸውን በማረጋገጥ ክሊራንስ ያዘጋጃል፣
- በማጣራት፣ በማስተላለፍና በማስወገድ ሂደት የወጡ ወጪዎችን በመመሪያ መሰረት እንዲተኩ ያደርጋል፣
- የተዘጉ ድርጅቶች ንብረት ወይም በስራ ላይ ያሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ለባለስልጣኑ በፍቃዳቸው የይወገድልን/ይተላለፍልን ጥያቄ ሲያቀርቡ በአዋጁ መሰረት እንዲተላለፍ/እንዲወገድ የውሳኔ ሃሳብ ያቀርባል፣ ሲፀድቅ ይፈጽማል፣
- የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈ እና ወደ ሌላ አካል ሊተላለፉ የማይችሉ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችንብረቶችን በህጉ መሰረት እንዲያቃጥሉ ወይም በመቅበር እንዲያስወግዱ ድጋፍ ያደርዳል፤
- እዳ ያለባቸው የተዘጉ ድርጅቶችን ንብረት ሰብስበው ለሌላ አካል መተላለፍ የማይችሉ ግን ቢሸጡ ዋጋ የሚያወጡ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ንብረት በጨረታ ለመሸጥ የንብረቶቹን የገበያ ዋጋ ግምት ያወጣል፣ ከአቅሙ በላይ የሆኑ ወይም ልዩ ሙያ የሚያስፈልጉትን የሙያ እገዛ ጥያቄ ለቡድን መሪው ያቀርባል፤
- የንብረት ሽያጭ ጨረታ ሰነድ ያዘጋጃል፣ በጨረታ አወጣጥ ሂደት ላይ በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋባዥነት ተሳታፊ ይሆናል፣
- የጨረታ ተወዳዳሪዎችን ትንተና የማመዛዘን ስራ ይሰራል፣ ለጨረታ አጽዳቂ ኮሚቴ የውሳኔ ሃሳብ ያቀርባል፣
- የተዘጉ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች አመራሮች ሲሰሩበት የነበረውን የህዝብ ንብረት በአግባቡ አስረክበው ማጠናቀቃቸውን በማረጋገጥ ክሊራንስ አዘጋጅቶ ያቀርባል፣
- የሚሸጡ ንብረቶችን የቀረጥ ነፃ መጠቀሚያ መብት ጊዜ ማለፉንና አለማለፉን የማረጋገጥ ተግባር ይመረምራል፣
- የባለመብቶችን የይገባኛል ጥያቄ መርምሮ ለቡድን መሪው ወይም ለዳይሬክቶሬቱ የውሳኔ ሃሳብ ያቀርባል፣
- የንብረት ማጣራት፤ ማስተላለፍና ማስወገድ ስራ ቀልጣፋ ለማድረግና የሚያጋጥሙትን ችግሮች ለመፍታት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት ይሠራል፤