አገልግሎቶች

ጥናትና ምርምር

  • የሲቪል ማሀበረሰብ ድርጅቶች አላማና የህብረተሰቡን ጥቅም የሚጎዳ የስጋት ምንጮችን በጥናት ይለያል፣
  • በፖሊሲ አፈጻጸም ላይ ያሉ የአሰራርና የአደረጃጀት ማነቆዎችን ተለይተው እንዲጠኑና መፍትሄዎች እንዲቀርቡ ያደርጋል፤
  • የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እሴት ግንባታ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች መሰረታዊ ለውጥ በሚያመጣ፣ በተደራጀ ሁኔታ ለማስፈጸም የሚያስችል ጥናትያደርጋል፣
  • የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የሚያፈሩት ሀብትና ንብረት (ፈንድ) ለማህበረሰቡ በተገቢው መንገድ ጥቅም ላይ መዋሉና ተደራሽ መሆኑን የሚያመላክቱምርምርና ጥናታዊ ጽሁፎችን ያከናውናል፤
  • ኅብረተሰቡን ወደ ተጠቃሚነት የሚያመራ የመፍትሄ አቅጣጫዎች የሚያመለክት ጥናት ያቀርባል፣
  • ለፖሊሲ አፈጻጸም ግምገማ ጥናት የሚያስፈልጉ መረጃዎች ይሰበስባል፣ ያደራጃል፣ እንዲሰበሰቡና እንዲደራጁ ያደርጋል፤
  • በኤጀንሲው፣ በክልል መንግስታት፣ በዘርፍ አስተዳደር እና በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ግንኙነትን የሚያጠናክሩ ጥናቶችን ያካሂዳል፣ የተገኙ ግኝቶች በስራላይ የሚውሉበትን መንገድ ያመቻቻል፣
  • በሀገሪቱ ውሰጥ የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ቁጥር፣ የሚንቀሳቀሱባቸው ክልሎችና የስራዘ ርፎች፣ የተጠቃሚው የህብረተሰብ ብዛት እና የአባሎቻቸው ቁጥር፣የሚያንቀሳቅሱትን ሀብት፣ የድርጅቶች ፕሮጀክት ስርጭት እና ተያያዥ ጉዳዮችን በጥናት ለይቶ ለመረጃ ፈላጊዎች ተደራሽ ያደርጋል፣ የመፍትሄ አቅጣጫያመላክታል፤
  • የፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች አፈጻጸም የውጤታማነት ትንተናበ ማድረግ ለፖሊሲ ግብዓት የሚሆኑ ጉዳዮችን ይለያል፣ የውሳኔ ሀሳብ ያቀርባል፤