ተግባርና ኃላፊነት

 • የጥናት አካባቢዎች መለየት፣ ዕቅድ ማቀድ፣ ክትትል ማድረግ፤
 • በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ ውስጥ ያለውን አሰራር ለማዘመን የአገልግሎት አሰጣጥ ፈጣን እና ቀልጣፋ እንዲሆን ለማድረግ የሚያስችል ጥናት ማካሄድ፤
 • በጥናትና ምርምር በተገኙ ውጤቶች መሰረት የተለያዩ የአሰራር ለውጦችን ተከትሎ ማሻሻያዎች እንዲደረጉ ግብዓት ማቅረብ፤
 • የሲቪል ማሀበረሰብ ድርጅቶች አላማና የህብረተሰቡን ጥቅም የሚጎዳ የስጋት ምንጮችን በጥናት መለየት፤
 • የኤጀንሲውን ክፍተቶች በጥናት በመለየት የአሰራር ስርዓቱ እንዲሻሻል የጥናት ውጤት ለሚመለከተው ክፍል ማቅረብ፤
 • በፖሊሲ አፈጻጸም ላይ ያሉ የአሰራርና የአደረጃጀት ማነቆዎች ተለይተው እንዲጠኑና መፍትሄዎች እንዲቀርቡ ማድረግ፤
 • የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች እሴት ግንባታ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች መሰረታዊ ለውጥ በሚያመጣ፣ በተደራጀ ሁኔታ ለማስፈጸም የሚያስችል ጥናት ማድረግ፣
 • በኤጀንሲው፣ በክልል መንግስታት፣ በዘርፍ አስተዳደር እና በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ግንኙነትን የሚያጠናክሩ ጥናቶችን ያካሂዳል፣ የተገኙ ግኝቶች በስራ ላይ የሚውሉበትን መንገድ ማመቻቸት፤
 • የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የሚያፈሩት ሀብትና ንብረት (ፈንድ) ለማህበረሰቡ በተገቢው መንገድ ጥቅም ላይ መዋሉንና ተደራሽ መሆኑን የሚያመላክቱ ምርምርና ጥናታዊ ጽሁፎችን ማከናወን፤
 • በፌዴራልና በክልል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች አስፈላጊነትና አወቃቀር ላይ የጋራ መግባባት ሊፈጥሩ የሚያስችሉ ሁኔታዎችን በጥናት መለየት፣
 • በሀገሪቷ ውሰጥ የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ቁጥር፣ የሚንቀሳቀሱባቸው ክልሎችና የስራ ዘርፎች፣ የተጠቃሚው የህብረተሰብ ብዛት እና የአባሎቻቸው ቁጥር፣ የሚያንቀሳቅሱትን ሀብት፣ የድርጅቶች ፕሮጀክት ስርጭት እና ተያያዥ ጉዳዮችን ማጥናት፤
 • በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በየአካባቢው የሚሰሩ የልማት ስራዎች እንደየዘርፋቸው በጥናት መለየት፤
 • ኅብረተሰቡን ወደ ተጠቃሚነት የሚያመራ የመፍትሄ አቅጣጫዎች የሚያመለክት ጥናት ማቅረብ፤
 • በኤጀንሲው ስር የተካሄዱ ፕሮጀክቶች/ፕሮግራሞች ያስገኙት ጠቀሜታ /impact/ እንዲገመገም ማድረግ፤
 • የፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች አፈጻጸም የውጤታማነት ትንተና በማድረግ ለፖሊሲ ግብዓት የሚሆኑ ጉዳዮችን ይለያል፣ የውሳኔ ሀሳብ ማቅረብ፤
 • ለፖሊሲ አፈጻጸም ግምገማ ጥናት የሚያስፈልጉ መረጃዎች እንዲሰበሰቡና እንዲደራጁ ማድረግ፤
 • ለፖሊሲ ቀረጻና ምርምር የሚያስፈልጉ ጽሁፎች ተለይተው እንዲጠኑ መረጃዎች እንዲሰበሰቡና እንዲደራጁ ማድረግ፤
 • ለሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የሚሰጡ ልዩ ልዩ ድጋፎች ውጤታማ እንዲሆኑ ክፍተቶቹን ጥናት ማድረግ፤
 • ድርጅቶች የሚያከናውኗቸው የልማት ስራዎች መንግሰት ከሚያወጣቸው የልማት ዕቅዶች ጋር የተጣጣሙ እንዲሆኑ የሚያግዙ ጥናቶችን ማከሄድ፤
 • ድርጅቶቹ በሀገሪቷ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ፣ ሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ እና የልማት እንቅስቃሴ ያላቸውን ሚና አስመልከቶ ተገቢውን ጥናት የማድረግ ስራ መስራት፤
 • ከሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጋር በተያያዘ ያሉ የኢኮኖሚ ሻጥሮችንና የሀብት ስወራዎች በሀገር ደረጃ ያላቸው ሥፋት፤ ጥልቀት እና ያስከተሉት ጉዳት ላይ ጥናት ማካሄድ እና
 • የተለዩ ዘርፎች በየትኛው የህበረተሰብ ክፍል ወይም ተቋም (መንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት) ሊከናወኑ/ሊደገፉ እንደሚገባ ማጥናት/መለየት፡፡