የባለስልጣኑ ስልጣንና ተግባራት በዝርዝር
- ድርጅቶችን መመዝገብ፣መደገፍ፣ስራቸውን ማሳለጥና ማስተባበር፤
- ድርጅቶች ስራቸውን በህግ አግባብ ማከናወናቸውን ለማረጋገጥ አስፈላጊውን ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ፤
- የድርጅቶችን ዓመታዊ የስራና የገንዘብ እንቅስቃሴ ሪፖርት በዚህ ሕግ በተወሰነው መሰረት መመርመር፤
- ድርጅቶች ግልጽነትና ተጠያቂነትን የሚያረጋግጥ የውስጥ አስተዳድር እና የራስ አስተዳድር ስርዓት እንዲኖራቸው አስፈላጊውን ድጋፍ መስጠትና ተፈጻሚነቱን መከታተል፤
- ከሚመለከተቸው የክልል መንግስታት አካላት ጋር በመተባበር በአገሪቱ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶችን ቁጥር፣ተሰማሩባቸውን እና የአባሎቻቸውን ብዛት እና መሰል መረጃዎችን የሚይዝ የመረጃ ማዕከል ማቋቋም እንዲሁም እነዚህን መረጃዎች መተንተን እና በጋዜጣና በድረ-ገጽ አሳትሞ ማሰራጨት፤
- ከፌደራልና ከክልል የመንግስት አካላት እንዲሁም ከድርጅቶች ጋር ቋሚ የምክክር መድረኮችን ማዘጋጀት፤
- ኃላፊነቱን ለመወጣት ከዘርፍ አስተዳዳሪዎች ጋር በትብብር መስራት፤
- ድርጅቶች መንግስት በሚያወጣቸው ፖሊሲዎች ሕጎች የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ማበረታታት፤
- ድርጅቶች በአገሪቱ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ፣ሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ እና የልማት አንቅስቃሴ ያላቸውን ሚና አስመልክቶ ተገቢውን ጥናት ማካሄድና መንግስት ማማከር፤
- ድርጅቶች የሚያከናውኗቸውን የልማት ስራዎች መንግስት ከሚያወጣቸው የልማት ዕቅዶች ጋር የተጣጣሙ እነዲሆኑ የሚያግዙ የፖሊሲ መመሪያዎችን ማዘጋጀት፤
- አግባብነት ባላቸው ሕጎች ስለሰነዶች ማረጋገጥና ምዝገባ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ የድርጅቶችን መተዳደሪያ ደንቦችና ማሻሻያዎቻቸውን ማረጋገጥና መመዝገብ፤
- የአገልግሎት ክፍያዎችን በዚህ አዋጅ መሰረት በሚወጣ ደንብ መሰብሰብ፤
- የንብረት ባለቤት መሆን፣ውል መዋዋል፣በራሱ ስም መክሰስ እና መከሰስ፤
- አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው በዚህ አዋጅ ተሰጡትን ስልጣንና ተግባራት ለሌሎች አካላት በውክልና መስጠት፤
- አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው በየትኛውም የአገሪቱ ክፍል ቅርንጫፍ መስሪያ ቤቶችን መክፍት፤
- በዘርፉ በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረትን ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን ለመከላከል የሚያስችሉ ስራዎችን ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር በትብብር መስራት፤
- ድርጅቶች ሲፈርሱ በሒሳብ አጣሪነት የሚያገለግሉ ባለሙያዎችን ዝርዝር ማዘጋጀትና ስራዎችን ባግባቡ መከናወናቸውን መቆጣጠር፤
- በአዋጅ የተቋቋመውን የሲቪል ማህበረሰብ ፈንድ ማስተዳደር፤
- የበጎ ፍቃደኝነትን ባህልና እንቅስቀቃሴ ማበረታታት፤የበጎ ፍቃደኝነት በተመለከተ የስርጸት ስራ መስራት፤
- ዓላማውን ለማስፈጸም የሚያስፈልጉ ሌሎች ተግባራትን ማከናወን፤