የበጐ ፈቃድ ማጐልበትና ትብብር መሪ ስራ አስፈጻሚ የሚሰጡ አገልግሎቶች
የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በኢትዮጵያ
- የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ፅንሰ ሃሳብ ትርጓሜው እንደ ማህበረሰቡ የዕድገት ደረጃና ከባቢያዊ ሁኔታ የሚለያይሲሆን በዋነኛነት ሰዎች/ ግለሰቦች ከሰብዓዊነት አመለካከት ተነስተው ለሚኖሩበት ማህበረሰብ ልማትናለአካባቢ ደህንነት በነጻ ጊዜያቸውን፣ ገንዘባቸውን፣ጉልበታቸውን፣ እውቀታቸውንና በጐ አመለካከታቸውንየሚያውሉበት በምላሹም ትምህርትና የህይዎት ልምድ እንዲቀስሙ የሚያስችላቸው ተግባር ነው፡፡
- ሀገራችን ኢትዮጵያም በዚሁ መከራው/ ችግሩ ሞልቶ በተረፈባት ምድር ላይ የምትገኝ ይልቁንም የችግር መዓትበተከማቸባት አህጉራችን አፍሪካ ውስጥ ያለች በመሆኗ የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን በጥብቅ ከሚሹ ሀገራትአንዷ ነች።
- ኢትዮጵያ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የመስጠት ባህል የነበራትና በፍጹም ወንድማማችነት ዜጎች የሚኖሩባትችግራቸውን በጋራ በመተባባር የሚያሳልፉባት ሀገር ነች።
- ይህ በመስጠት የሚገለጸው በጎ ፈቃደኝነት የሀገሩ ባህል ነው።
- ልዩ ልዩ ዓይነት ልማድና ወግም ነበር።
- ሲወልድ የግምዶ፣ ሲያዝን የዝን ብሎ ከመስጠት ጀምሮ ሲዘምት የስንቅ፣ ሲመለስ የደስታ፣ ሲሻር የሹመትአይደንግጥ፣ ሲሾም የምስራች፣ ለሠርግ ሲጠራ ለጽም…. ብሎ እስከመስጠትም የረቀቀ ነው።
- ከምንም በላይ ግን ወርቃማ የነበረው ሲታመሙ የመጠየቂያ ብሎ ከመስጠት ጀምሮ ሲወረስ፣ ሲክስ፣ሲቃጠልበት፣ ሲቀማ… እርጥባን ብሎ መስጠት የተለመደ ነበር።/ፍኖተ አእምሮ፤ ልዑል ራስ ካሳ ኃይሉ፤ 1953 ዓ.ም/
- ለችግረኞች፣ ለአረጋውያን፣ ለእጓለ ማውታ ተሰብስቦ በደቦ ማረስ፣ መውቃት፣ ሰብስቦ ከጎተራ መክተቱ በግብርናኖሮ እዚህ ዘመን ድረስ ለዘለቀው ማኅብረሰብ እንግዳ ነገር አልነበረም።
- ካመረተው እህል ከፍሎ ከመስጠት ጀምሮ፣ በጉልበቱ፣ በሙያው ለችግረኞች መድረስን የሚያውቅ ሕዝብ ነው።
- ችግር ያጋጠማቸውን ሰዎች ቀስቃሽ ሳያስፈልግ ማገዝ የበጎ እሴቶቻችን አንድ አካል ነው።
- በተለይ በገጠር መንገድና ዘመናዊ የትራንስፖርት አገልግሎት ባልነበረበት ወቅት የታመሙ ሰዎችን በወሳንሳተሸክሞ ሩቅ አካባቢ ወስዶ ማሳከም የታማሚው ቤተሰቦች ብቻ ሳይሆኑ የሀገሬው/ የአርሶ አደሩ ድርሻ ነበር።
- ሙታንን መቅበርም እንደዚያው። ሕዝብ ተባብሮ የቀብር ጉድጓድ ቆፍሮ፣ አስከሬን ተሸክሞ የቀብር ሥነሥርአቱን ይፈጽማል። በኢትዮጵያ ሙታንን መቅበር እንደ ሌላው ዓለም የቤተሰብ እዳ ሆኖ አያውቅም።
- ማህብረሰቡ የጋራ ኃላፊነት የሚወስድባቸው እጅግ በርካታ ጉዳዮች ነበሩት። እንደ አሁኑ የአእምሮ ሕሙማንማሰባሰቢያ ሳይደራጅ፣ መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሳይገቡበት አካል ጉዳተኞችን እናየአእምሮ ህሙማንን መንከባከብ የጋራ ድርሻ ነበር።
- ኢትዮጵያውያን የበጎ ፍቃድ አገልግሎት የሚሰጡት በችግር ወቅት ብቻ አይደለም።
- ከላይ አስቀድመን እንደጠቀስነው በምርት ስራ ላይም በበጎ ፍቃድ አገልግሎት ይተጋገዛሉ።
- የደቦ ወይም ጂጊ ባህልን ለዚህ ማሳያነት መጥቀስ ይቻላል። ከቤተሰብ አቅም በላይ የሆነ የምርት ስራ ለምሳሌእርሻ፣ አጨዳ፣ ጎጆ ማዋቀር . . . ሲኖር መንደርተኛው በሙሉ የራሱን መሳሪያ ይዞ በስራ ይተባበራል። ለዚህመልካም ግብር የሚያዘነበል ሥነ ልቦናም ኢትዮጵያውያን አላቸው።
- በግላቸው ብቻ ሳይሆን ለበጎ ነገር በበጎ ፈቃድ በሀገር መሪዎች ጥሪ መዝመትንም ያውቁበታል።
- የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በተለይ በከፉ/በክፉ/ ቀናት እጅግ ወሳኝ ሚና ይጫወታል።
- በንጉሠ ነገሥት ምኒልክ ዘመን ተከስቶ በነበረው ክፉ ቀን በተባለው ብዙ እንስሳት ባለቁበት ዘመን አርሶመብላት፣ ዘርቶ መቃም ጭንቅ ነበር። በዚህም ምክንያት ሰዎች በረሃብ ረገፉ።
- የከብቱ ማለቅ ለሰው ማለቅ ተረፈ። በዚህ ጊዜ መላ የዘየዱት ንጉሠ ነገሥቱ የበጎ ፈቃድ አገልግሎትንበአርኣያነት ማሳየት ነበር። ማረሻ በሬ/ ከብት/ ባይኖርም እንኳን ራሳቸው ንጉሡ መጥረቢያ አስለው፣ መቆፈሪያአዋደው የሚቆረጠውን መቁረጥ የሚቆፈረውን መቆፈር ጀመሩ።
- በሰው ጉልበት ችግርን መወጣት እንደሚቻል ለማሳየትና መኳንንቱም መሳፍንቱም እርሳቸውን አይተውወርደው ሕዝቡን እንዲያገለግሉ ለማድረግ ጥረት አደረጉ። ንጉሡ እጅና እግራቸው በእሾህና ጋሬጣ እስኪደሙእስኪቆስሉ ከእንጦጦ ማርያም በታች ያለውን የኤካን ዱር ሁሉ ለማልማት ጥረው ነበር። በእርግጥም ትልቅትንሽ፣ ቄስ መነኩሴ ሳይል ሁሉም ተሰልፎ የሚገባውን ያደረገበትን የዚያን የክፉ ቀን ዘመቻ አፈወርቅገብረኢየሱስ በመጽሐፋቸው አውስተውታል።/ዳግማዊ አጤ ምኒሊክ፤ አፈወርቅ ገብረ ኢየሱስ፤1901 ዓ.ም/
- በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመንም ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ማኅበር ዘመናዊ የሆነውን የበጎ ፈቃደኞችአገልግሎት የበለጠ ባህል ለማድረግ በስፋት የተንቀሳቀሰበት ጊዜ ነበር። ዓለም አቀፍ በጎ ፈቃደኛ ወገኖችምሀገራችንን በመጎብኘት በህክምና እና በትምህርት መስክ ይሰጡ የነበረው አገልግሎት ለኢትዮጵያውያን ዘመናዊበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማደግ ብርቱ ተሞክሮዎች ነበሩ።
- በወታደራዊው ደርግ የስልጣን ዘመን ደግሞ ምንም እንኳን የተወሰነ አስገዳጅነት ቢኖረውም በ1967 ዓ/ምየሁለተኛ ደረጃና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን የተሳተፉበት የእድገት በህብረት ዘመቻ እንደ በጎ ፍቃድአገልግሎት ልምምድ የሚታይ ነበር።
- ላለፉት በርካታ ዓመታት በሀገራችን ይደረጉ የነበሩ የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶችም ልማታዊ ሥራዎችንከማስፋፋት አንጻር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ነበራቸው። በአብዛኛው የማጠናከሪያ ትምህርት በመስጠትና በመንገድትራፊክ ቁጥጥር ሥራዎች ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሲያደርጉ ነበር።
- ከ2010 የክረምት ወራት ጀምሮ እጅግ በተለየ መንገድ በፖሊሲ የሚመራ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እንዲስፋፋበክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካኝነት ሰፋፊ ዘመቻዎች ተጀምረዋል።
- የአረጋውያንን ቤቶች በመጠገን፣ ችግረኛ ተማሪዎችን በመርዳት፣ ደም በመለገስ ወዘተ ራሳቸው ጠቅላይሚኒስትሩ የጀመሯቸውን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራዎች ሌሎች የማኅበረሰቡ ክፍሎችም ተከትለውለማስፋፋት ጥረዋል።
- የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ኤጀንሲም የበጎ ፍቃድና በጎ አድራጊነትን ባህል ማድረግ የሚል ስልጣን በአዋጅከተሰጠው ጊዜ አንስቶ በርካታ መዋቅራቂ፣ የገንዛቤና ንቅናቄ እንዲሁም ስርዓት ዝርጋታ ስራዎችን በመስራትላይ ይገኛል፡፡