ተግባርና ኃላፊነት

 • በተቋሙ ውስጥ ለሙስናና ብልሹ አሰራር ክፍተት የሚፈጥሩ ጉዳዮችን ለመለየት የሚያስችሉ ጥናቶችን ማካሄድ፤ መለየት፤
 • ከሌሎች የሥራ ክፍሎች ጋር ያለውን ቅንጅት እና ትስስር በማጥናት የተጠናከረና ተመጋጋቢነት ያለው የስራ ግንኙነት እንዲፈጠር ሁኔታዎችን ማመቻቸት፤ አፈጻጸሙን መከታተል መደገፍ፤
 • የአሰራር ክፍተቶችን ሊያሟላ የሚችል ተቋማዊ ረቂቅ የስነ-ምግባርና የብልሹ አሰራር ማንዋል ማዘጋጀት፤
 • ከስነ-ምግባር ጉድለትና ከሙስና ጋር በተያያዘ የጥቆማ የአቅራቢዎች ሚስጢራዊነት ሊያረጋግጥ የሚችል የአሰራር ስርዓት ማዘጋጀት፤
 • የስነ-ምግባር ተግባራትን የሚያጎለብቱ አሰራሮችን ሊያሻሽሉ የሚችሉ ጉዳዮች ላይ በየወቅቱ ጥናት ማካሄድ፤ ለሚመለከተው አካል ማቅረብ፤
 • የተቋሙን ሰራተኞች የስነምግባር አስተሳሰባቸውን ሊያጎለብቱ የሚችሉ የስልጠና ሰነዶችን ማዘጋጀት፤ ስልጠና መስጠት፤
 • በተቋሙ የስነ-ምግባርና የጸረ-ሙስና የአሰራር ማንዋልና የመተዳደሪያ ደንብ(Code of Conduct) ማዘጋጀት፤ ስልጠና መስጠት፤
 • ሀገር አቀፍ የስነ-ምግባርና የጸረ-ሙስና ፖሊሲዎች፣ ደንቦች እና መመሪያዎች ዙሪያ ለተቋሙ ሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን መስጠት፤
 • በተቋሙ ውስጥ ሃብታቸውንና የገንዘብ ጥቅማቸውን እንዲያስመዘግቡ የህግ ግዴታ ለተጣለባቸው ሰራተኞችና ሃላፊዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በመስጠት ሀብታቸውን በአግባቡ እንዲያስመዘግቡ ማድረግ፤ በአግባቡ መመዝገብ፤
 • የስነ-ምግባር ተግባራትን የሚያጎለብቱ ተሞክሮዎችን መቀመር፤ ማስፋፋት፤ አሰራሮችን በየወቅቱ ማሻሻል፤
 • የተቋሙ የስነ-ምግባርና የጸረ-ሙስና የአሰራር ማንዋልና የመተዳደሪያ ደንብ(Code of Conduct) እንዲሁም የሀገሪቱ የስነ-ምግባር የጸረ-ሙስና ህጎችና መመሪያዎች በተቋሙ ውስጥ መከበራቸውን መከታተል፤
 • በክትትል ወቅት የተገኙ የአሰራር ክፍተቶች በመለየት የመፍትሄ ሃሳብ ለሃላፊው ማቅረብ፤
 • በስነ-ምግባርናበጸረ-ሙስና ፖሊሲዎች፣ ደንቦችና መመሪያዎች ዙሪያ የተሰጡ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች ያመጡትን ለውጥ መከታተል፤
 • ሠራተኞች የሚያቀርቧቸውን የስነ-ምግባር ችግሮችና ማንኛውም ደንብና መመሪያ ጥሰት ጥቆማዎችን ተቀብሎ ምርመራ ማድረግ፤ የማስተካከያ እርምጃ በመለየት ለውሳኔ ሃላፊው ማቅረብ እና
 • በስነ-ምግባር ጉድለት ምክንያት በተከሰቱ ችግሮች ላይ የተወሰዱ ዕርምጃዎችን መከታተል፡፡