ተግባርና ኃላፊነት

 • በኤጀንሲው ውስጥ የሴቶችና ወጣቶች እኩል ተሳታፊነትና ተጠቃሚነትለማረጋገጥ፣ እንዲሁም የህጻናት መብትና ደህንነትን ለማስጠበቅ የአሰራር ሥርዓትመዘርጋት፤
 • የተለያዩ ሰነዶችን ከሴቶችና ወጣቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት፣ እንዲሁም ከህጻናት መብትና ደህንነት አጠባባቅ አኳያ በመገምገምና ተገቢውን ግብአት በመስጠት ተግባራዊ እንዲሆን ማድረግ፣ ማስተባበር፤
 • ከመ/ቤቱ ተግባርና ኃላፊነት አኳያ በሴቶችና ወጣቶች ተጠቃሚነት እና ከሕጻናት መብትና ደህንነት በማስጠበቅ ዙሪያ የተለያዩ ጥናቶችና ምርምር ሥራዎችን ማካሄድ፣ ከሌሎች የሥራ ክፍሎች ጋር በጋራ በሚከናወኑ ጥናቶችም ላይ በባለቤትነት ማሳተፍ፤
 • ሴቶችና ወጣት ሰራተኞች በስራ ቦታ ከአደጋና ከጉልበት ብዝበዛ የሚጠበቁበት ሁኔታ እያጠና ተግባራዊ ማድረግ፤
 • ሴቶች፣ ህፃናት እና ወጣቶች ላይ የሚፈጸሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን መደገፍ፣ ማስተባበር፤
 • በመ/ቤቱ በተቋቋመው የህጻናት ማቆያ የሚገኙ ህጻናት በተዘጋጀው ስታንደርድ መሰረት ህጻናቱ ጤናቸውና ስብእናቸው ተጠብቆ በማቆያው ውስጥ እንዲቆዩ ለማድረግ የተመደቡ ባለሙያዎችን ማስተባበር፣ አስፈላጊ ባለሙያዎችና ቁሳቁሶች እንዲሟሉ ክትትል ማድረግ፣ እንዲሁም ባለሙያዎቹ ተገቢውን ስልጠና እንዲያገኙ ማድረግ፣
 • በመስሪያ ቤቱ ያሉ የሴት አደረጃጀቶችን አቅም ለማጐልበትና በቅንጅት ለመስራት የሚያስችል ስልት መቀየስ፣ ሲፈቀድም ተግባራዊ ማድረግ፣
 • ለሴት ሠራተኞች ፍላጐትን መሠረት ያደረገ የአጭርና የረጅም ጊዜ ሥልጠና በሴክተሩአመታዊ እቅድ ውስጥ እንዲካተት ማድረግ፤
 • ሴቶች፣ ህፃናት እና ወጣቶችን አስመልክቶ የተዘጋጁ ህጐች፣ ፖሊሲዎች፣ የአፈፃፀም ማኑዋሎች፣ የሥራ መመሪያዎች፣ ሀገራችን ስምምነት የገባችባቸው ዓለም አቀፍና አህጉራዊ ስምምነቶች ላይ ተከታታይ የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎች በመስሪያ ቤቱ ለሚገኙ አመራሮችና ባለሙያዎች ስልጠና መስጠት እንዲሁም ያስገኘውን ፋይዳ መገምገም፤
 • ሴቶች፣ ህፃናት እና ወጣቶች ጉዳይ ዙሪያ የግንዘቤ ማስጨበጫና የንቅናቄ ስራዎችን ማስተባበር፤
 • በፍላጐት ላይ የተመሰረተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ኘሮግራም ተከታታይነት ባለው መልኩ ለመሥራት እንዲቻል የዳሰሳ ጥናት ያካሂዳል፣በጥናቱ ግኝት መሰረት የአመለካከት ለውጥ ለማምጣት የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልቶችን ይቀይሳል፣ ሲፈቀድም ተግባራዊ እንዲሆን ማድረግ፤
 • በመ/ቤቱ ባሉ ዳይሬክቶሬቶች እና ስራ ክፍሎች የሚዘጋጁና የሚተገበሩ እቅድና ሪፖርት የሴቶችን፣ የህጻናትን እና ወጣቶች ጉዳይ ማካተታቸውን በመገምገም ደረጃውን የጠበቀ ወቅታዊ ግብረ-መልስ ማስተባበር እና
 • ሴቶች፣ ህፃናት እና ወጣቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማጐልበት፣ እንዲሁም የህጻናትን መብትና ደህንነት ለማስጠበቅ በመስሪያቤቱ የሚደረገውን ክትትል፣ ድጋፍና ሱፐርቪዥን ማስተባበር፡፡