ተግባርና ኃላፊነት

 • በመንግሥት ሠራተኞች መመሪያዎችና ደንቦች መሠረት አደረጃጀት ላለው ተቋም  ልዩ ልዩ የቅጥር፣ የደረጃ ዕድገት፣ ዝውውር፣ የዲስፕሊን፣ የቅሬታ ማስተናገጃና ሌሎች አግባብነት ያላቸው  ኮሚቴዎች እንዲቋቋሙና ተግባራዊ እንዲሆኑ መከታተል፤
 • አዲስ ለሚቀጠሩ ሠራተኞች ስለ መንግሥት መመሪያዎችና ደንቦች እንዲሁም ተቋሙ ስለተቋቋመበትና ስለሚጠበቅበት ውጤት ስለ መሥሪያ ቤቱ ልዩ ልዩ የሥራ ክፍሎች ኃላፊነት የማስተዋወቂያ ስልጠና (`Induction) እንዲሰጥ በማድረግ ወደ ሥራ እንዲሰማሩ ማድረግ፤
 • ለዳይሬክቶሬቱ የሚያስፈልጉ ለአቅም ግንባታ ስራዎች፤ለትምህርት፤ ለህትመት፤ለግዥና ተያያዥ ተገቢውን በጀት በማስፍቀድ ተግባራዊ ማድረግ፤
 • የዳይሬክቶሬቱን ወቅታዊ የሥራ አፈጻጸም ለበላይ አካል ሪፖርት ማቅረብ፤
 • አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ አደረጃጀት ላለው ተቋም የሰው ሀብት ሥራ አመራርን የተመለከቱ የውስጥ መመሪያዎች እንዲወጡ፤ እንዲከለሱና አዳዲስ ጥናት እንዲጠኑ ማድረግ፣ የጥናት ውጤቶችን መገምገም፤
 • አደረጃጀት ላለው ተቋም ለሥራ መደቦች የሥራ ትንተና ተከናውኖ የሥራ ዝርዝር መግለጫ እንዲዘጋጅ ማድረግ፤
 • አደረጃጀት ላለው ተቋም ደረጃውን የጠበቀ የሰው ሃብት የሥራ አካባቢ ደህንነትና ጤንነት ጥበቃ ጥናቶች እንዲጠኑ ማድረግ፣ የተጠኑትን መገምገም፣ ለሚመለከተው አካል ማቅረብ፤
 • የኤንሲው ሰራተኞች ስራዎቻቸውን በአግባቡ ማከናወናቸውን መከታተልና ተገቢውን ጥናት ማካሄድ፤
 • መልካም ተሞክሮዎችን በመቀመር ዳይሬክቶሬቱ የሚመራበትን አዳዲስ አሰራሮች በመቀየስና በመገምገም የአሰራር ስርዓት መዘርጋት፤
 • የሰው ሀብት ሥራ አመራር የስምሪት ሥራዎች በደንብ እና መመሪያ መሠረት እንዲተገበሩ ማድረግ፤
 • የመንግሥት ሠራተኞች አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ ሰርኩላሮች እና አግባብነት ያላቸው መመሪያዎችን ተፈጻሚነታቸውን መከታተል፤
 • አደረጃጀት ላለው ተቋም ሜሪቲን የተከተለ የሰው ሀብት ምልመላና መረጣ እንዲከናወን ማድረግ፤
 • የኤጀንሲውን ሰራተኞች ልዩ ልዩ ጥቅማጥቅሞችና አገልግሎቶች አሰጣጥ ሳይዛቡ ሥራ ላይ እንዲውሉና በወቅቱ ተግባራዊ እንዲሆን ማድረግ፤
 • የሠራተኛ የግል ማህደሮችና ማንኛውንም ሰራተኛን የሚመለከቱ መረጃ ተሟልተውና ዘመናዊ ሆነው እንዲያዙ ክትትል ማድረግ፤
 • የሰው ኃይል እቅድ መረጃዎች እንዲሰበሰቡ፣ እንዲደራጁ ተተንትነው እንዲጠናቀሩ ያደርጋል፣ የመረጃዎችን ትክክለኝነት ያረጋግጣል፣ ለሚመለከተው አካል ያስተላልፋል፤
 • በደረጃው ለተፈቀዱ የስራ መደቦች የሰው ኃይል ስምሪት ፈተናዎችን ያዘጋጃል፣ በሚመለከታቸው የስራ ክፍሎችም እንዲዘጋጁ ያደርጋል፣ ይፈትናል፣ እንዲፈተኑ ያደርጋል፣ ያርማል፣ እንዲታረሙ ማድረግ፣መረጃዎቹን በዘመናዊ የመረጃ ዘዴ /በሃርድና በሶፍት ኮፒ/ ተደራጅተው እንዲያዙ ማድረግ፤
 • በዳይሬክቶሬቱ ስር የሚገኙ ሰራተኞች በባለቤትነት ስሜት እንዲሰሩና ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት እንዲሰጡ ያለባቸውን የአፈጻጸም ክፍተት ይለያል፣ እንዲበቁ ማድረግ፤
 • ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በሰው ሃብት ሥራ አመራር ዙሪያ ለሚቀርቡ ማብራሪያዎች ህጉን መሠረት በማድረግ ማብራሪያና ምላሽ ይሰጣል ተገቢውን ሙያዎ ድጋፍ ማድረግ፤
 • በስነ-ምግባር ጉድለት ምክንያት በተከሰቱ ችግሮች ላይ የተወሰዱ ዕርምጃዎችን መከታተል፤
 • ለመ/ቤቱ ተስማሚ የሆኑ ዘመናዊ የለውጥ ሥራ አመራርና የአሠራር ማሻሻያ ስልቶች ተለይተው እንዲቀርቡ ማድረግ፤
 • የለውጥና መልካም አስተዳደር ሥራዎች ቀጣይነትን የሚያረጋግጡ አዳዲስ የአሠራር ስርዓቶች በማጥናት፣ ምርጥ ተሞክሮዎችን በመቀመር ለመ/ቤቱ ጠቃሚ የሆኑትን ተግባራዊ ማድረግ፤
 • የሥራ ዘርፉን የአሰራር ችግሮች በመለየትና በማጥናት ምቹ የአሰራር ሂደት እንዲኖር ማድረግ፤
 • በተግባር ላይ እንዲውሉ የተመረጡ የለውጥና መልካም አስተዳደር ሥራዎች አተገባበር ከሁኔታዎች ጋር ተጣጥመው እንዲሰራባቸው ማድረግ እንዲሁም ስራ ላይ ማዋል፤
 • በመ/ቤቱ የሚገኙ የሥራ ዘርፎች በአስቀመጡት የለውጥና መልካም አስተዳደር ሥራዎች ግቦች እና እቅድ መሠረት መፈጸማቸውን ክትትል በማድረግ ለዳይሬክቶሬቱ ማቅረብ፤
 • በመ/ቤቱ የመልካም አስተዳደር ሥርዓት መስፈኑን መከታተል፤
 • በለውጥ አፈጻጸም ላይ የሚያጋጥሙ የአሠራር ችግሮችን በመለየት ማቅረብ፤
 • በመ/ቤቱ ተግባራዊ የሆኑ የለውጥና መልካም አስተዳደር ሥራዎች ያስገኙት ፋይዳ መከታተል፤
 • በሥራ ላይ እንዲውሉ ውሳኔ ያገኙ ልዩ ልዩ የጥናት ሰነዶች ተግባራዊ እንዲሆኑ ለተጠቃሚ ክፍሎች ማስተላለፍ፤
 • የለውጥና መልካም አስተዳደር ሥራዎች ከአፈጻጸም አኳያ ለመገምገም በተዘጋጀ ሪፖርት አቀራረብ ስርዓት ስለመቅረቡ መከታተል እና
 • የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ስለለውጥ 1. ዓላማዎች እንዲገነዘቡና የህዝብ አገልጋይነት ስሜት እንዲያዳብሩ የአመለካከት ለውጥ እንዲያመጡ ተከታታይነት ያላቸው የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች እንዲዘጋጁ ማድረግ፡፡