አገልግሎቶች
 • የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በፕሮጀክት ስምምነታቸው መሰረት አስፈላጊውን መስፈርት አሟልተው ሲቀርቡ የቀረጥ ነፃ ድጋፍ ደብዳቤ ፈርሞ ይሰጣል፣
 • የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በበጀት አመታቸው ለበጎአድራጎት ስራዎች ቫት ተጥሎባቸው የተገዙን ብረቶችና አገልግሎቶችን የቫት ተመላሽ ይመለስልን ጥያቄ ሲያቀርቡ የቫት ተመላሽ ድጋፍ ደብዳቤ ፈርሞይ ሰጣል፣
 • የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የውጭ ሀገር ዜጋ ስራ ፍቃድ ሲጠይቁ በፕሮጀክት ስምምነት ማካተታቸውን፣
 • የትምህርት ዝግጅታቸው በሀገር ውስጥ ባሉ ባለሙያዎች የማይሸፈንና የቴክኖሎጂ ሽግግር ያመጣል ተብሎ ሲታመን/ሲረጋገጥ የውጭ ሀገር ዜጋ ስራ ፍቃድ ድጋፍ ደብዳቤ ፈርሞ ይሰጣል፣
 • የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በፕሮጀክ ትስምምነታቸው መሰረት አስፈላጊውን መስፈርት አሟልተው ሲቀርቡ ለተሸከርካሪ የኮድ 35 ታርጋ ድጋፍ ደብዳቤ ፈርሞይ ሰጣል፣
 • የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የባንክ ሂሳብ ቁጥር እንዲከፍቱ እና እንዲያንቀሳቅሱ ፍቃድይሰጣል፣
 • የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ተጨማሪ ገቢ ለማመንጨት እንዲችሉ በገቢ ማስገኛ ስራ ለመሰማራት ጥያቄ ሲያቀርቡ ጥያቄያቸውን በማጣራት ድጋፍ ደብዳቤያ ዘጋጃል፣
 • የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ተጨማሪ ገቢ ለማመንጨት እንዲችሉ በህዝባዊ መዋጮ ስራዎች ለመሰማራት ጥያቄ ሲያቀርቡ ጥያቄያቸውን በማጣራት ድጋፍ ደብዳቤ ያዘጋጃል፣
 • የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ተጨማሪ ገቢ ለማመንጨት እንዲችሉ በወጪመጋራት ስራዎች ለመሰማራት ጥያቄ ሲያቀርቡ ጥያቄያቸውን በማጣራት ድጋፍ ደብዳቤ ያዘጋጃል፣
 • ለሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በአዋጅ ፣ደንብ እና መመሪያዎች ዙሪያ የህግ ምክር አገልግሎት ይሰጣል
 • የተሻለ አፈፃፀም ያላቸውን የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ይለያል ፣ ያበረታታል እንዲሸለሙ ያቀርባል፤
 • ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች መለየት እና እንደ አስፈላጊነቱ ለበላይ አመራሩ ያቀርባል፤
 • ለሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በአዋጅ፣ ደንብ እና መመሪያዎች መሰረት ስልጠናዎችን ይሰጣል
 • ከመንግስት ወይም ከኤጀንሲው የሚወጡ ፖሊሲዎችን ፣ ስትራቴጂዎች ፣ አዋጆች ፣ ደንቦች ፣ መመሪያዎችና የተለያዩ ማንዋሎች መተግበራቸውን መከታተል፤
 • ለሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች አስፈላጊውን መስፈርቶች አሟልተው ሲቀርቡ የተለያዩ የድጋፍ ደብዳቤዎች መስጠት ማለትም / የቀረጥ ነፃ ፣ ቫት ተመላሽ ፣ የውጭ ዜጋ ስራ ፍቃድ ፣ ኮድ 35 ፣ የስራ አስኪያጅና ስራ አመራሮች ማረጋገጫ ደብዳቤ መስጠት፣
 • የባንክ ሂሳብ ቁጥር እንዲከፍቱ እና እንዲያንቀሳቅሱ ፍቃድ መስጠት ፣ እንደ አስፈላጊነቱ የገቢ ማስገኛና የህዝባዊ መዋጮ ድጋፍ ደብዳቤ መጻፍ፤
 • ከህግ ውጭ ለወንጀል ድርጊት አስበው የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ በማቅረብና ለሽብርተኝነት ዓላማ ለማዋል ተብሎ የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶችን በቅርበት በመከታተል የገንዘብ እና የንብረት ምንጩን የማጣራት ስራ መስራት፤
 • በማጣራት ሂደት የተገኙ መረጃዎችን መሰረት በማድረግ ህግ ተላልፈው በተገኙ አካላት ላይ ተገቢው እርምጃ እንዲወሰድ ከሚመለታቸው የመንግሰት አካላት ጋር በትብብር መስራት፤
 • የተለያዩ ሚዲያዎችንና ሌሎች ዘዴዎችን በመጠቀም ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ለሰብዓዊ ዕርዳታ ተብሎ የመጣ ገንዘብ ለሽብርተኝነት ተግባር እንዳይውል የግንዛቤ ማስጨበጫ መስራት፤
 • ማንኛውም የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት ከየትኛውም ምንጭ የሚያገኘውን ገንዘብ ለኤጀንሲው እንዲያሳውቅ የማድረግ መስራት፤
 • ድርጅቶች በተፈራረሙበት የፕሮጀክት ስምምነት መሰረት ያቀዱትን ገንዘብ ስራ ላይማዋላቸውን ክትትል ማድረግ፤
 • ማንኛውም የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት የበጀት ዓመቱ ሲጠናቀቅ በውጭ ኦዲተር አስመርምሮ የሚያቀርበውን የየዓመቱን የኦዲት እና አመታዊ የስራ ክንውን ሪፖርት መገምገም፤
 • በኦዲት እና የስራ ክንውን ሪፖርት ላይ ያሉ አጠቃላይ ሂደቶች ዙሪያ ለድርጅቶች አጠቃላይ ግብረመልስ መስጠት፤
 • በቀረቡት የኦዲት እና የስራ ክንውን ሪፖርት ላይ የህግ ጥሰቶች ሲያጋጥሙ እንደችግሩ ክብደት ከሚመለከተው የዘርፍ አስተዳደር ጋር በመነጋገር የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ ለሚመለከተው የበላይ ኃላፊ ከተገቢው መረጃ ጋር የውሳኔ ሀሳብ ማቅረብ፤
 • የሂሳብ ሰነዶቹ የሂሳብ አመቱ ካለቀ በኋላ ቢያን ስለ 5 ዓመት ተጠብቀው መቆየታቸውን ክትትል ማድረግ፤
 • የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የውስጥ አሰራራቸው ግልፀኝነትና ተጠያቂነት ባለው ሁኔታ እያከናወኑ መሆናቸውን የራስ-በራስ አስተዳደር ስርዓትን በህጉ መሰረት ተግባራዊ ማድረጋቸውን ተገቢውን ክትትል ማድረግ፤
 • የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የሚያደርጓቸውን ለውጦች (የአድራሻ ፣ የአመራር ፣ የስያሜ…) ማሳወቃቸውን መከታተል፤
 • የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቱ መደበኛ ሪፖርት ማድረጊያ ጊዜው ከ 3 ወር በላይ ከቆየ የሲቪል ማህበረሰቡ ድርጅቱን በጋዜጣ ጥሪ በማድረግ የህልውና ማረጋገጥ ስራ መስራት፤
 • የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በአዋጅ ደንብ እና መመሪያዎች መሰረት ህጋዊ የባንክ ሂሳብ መክፈታቸውንናየ ገንዘብ እንቅስቃሴያቸውም በተከፈተው ህጋዊ የባንክ ሂሳብ መሆኑን ማረጋገጥ፤
 • ማንኛውም ድርጅት አግባብ ባለው ህግ መሰረት ከተገቢ የስራ ፍቃድ ውጭ የውጭ ሀገር ዜጎችን አለመቅጠራቸውን መከታተል ፣ ማረጋገጥ ፤
 • በድርጅቶቹ መደበኛ ደመወዝ ሳይከፍላቸው በሙያቸው በበጎፍቃደኝነት ከአንድ አመት ላልበለጠ ጊዜ ለማገልገል የሚመጡ የውጭ ሀገር ዜጎችን የድርጅቱን አላማ ለመደገፍ መምጣታቸውን ማረጋገጥ፤
 • ድርጅቶች በተቋቋሙበት አላማ መሰረት እየሰሩ መሆኑን ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ፤
 • የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የገንዘብ እንቅስቃሴ የሚያሳይ ተቀባይነት ባለው የሂሳብ አሰራር በተዘጋጀየ ሒሳብ መዝገብ እንዲይዙ መከታተል፤
 • የሂሳብ ሰነዶቹ የድርጅቱን ገቢና ወጪ ፣ የወጪው ምክንያት ፣ ሀብትና እዳ ፣ የለጋሾችን ማንነትና የገቢውን ምንጭ ያካተተ ስለመሆኑ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፤
 • ኤጀንሲው ከመንግስት አካላት ፣ ከለጋሽ ድርጅቶች ወይም ከህዝብ ከሚቀርብ ጥቆማዎች ወይም ኤጀንሲው ስራውን በሚያከናውንበት ወቅት ከሚገኙ መረጃዎች በመነሳት የህግ ጥሰቶች የማጣራት እና የመቆጣጠር ተግባር መስራት፣
 • ከዘርፍ አስተዳደሪዎች ጋር ኤጀንሲው ኃላፊነቱንለ መወጣት ድርጅቶች ፕሮጀክት መፈራረማቸውን በመከታተል ፣ በተፈረመው ፕሮጀክት መሰረት ስለመተግበራቸው ማረጋገጥ ፣ ፕሮጀክቶቹ ሲጠናቀቁ ወይም ሲቋረጡ ሴክተሩን አስመልከቶ እንዴት ማስቀጠል እንዳለበት ሂደቱን ማመቻቸት ፣ ተያያዥ ንብረቶችን በተመለከተ ተባብሮ መወሰን ፣ የተለያዩ ተያያዥ ድጋፎችን መስጠት እንዲሁም የፕሮጀክቶች ጊዜ ሲጠናቀቅ የማጠቃለያ ግምገማ መደረጉን የማረጋገጥ ስራ መስራት፤
 • የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በራሳቸው ፈቃድ እንዲሰረዙ ጥያቄ ሲያቀርቡ ወይም በህጉ መሰረት ለመሰረዝ የሚያበቁ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ የምዝገባ ሰርተፍኬታቸው እንዲሰረዝ የውሳኔ ኃሳብ ለበላይ አመራሩ ማቅረብ፤