አገልግሎቶች

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ንብረት አስተዳደደር ዳይሬክቶሬት

ከዳይሬክቶሬቱ የሚጠበቁ ውጤቶችና ተግባራት፡-

 • ተገልጋዮች ፈጣን እና ጥራት ያለው አገልግሎት ማግኘታቸውን በየጊዜው መረጃዎችን ሰብስቦ የሚያጋጥሙ ችግሮችንና ቅሬታዎችን እየተከታተለ የዳይሬክቶሬቱን እቅድ ያዘጋጃል፣ እቅዱ በተገቢው በጀት መደገፉን ያረጋግጣል፣ አፈጻጸሙን በየጊዜው መገምገም እንዲሁም በስሩ ለሚገኙ ሰራተኞች የተቋሙን ራዕይ፣ ተልዕኮ እና ስትራቴጂክ ግቦች ያስተዋውቃል፤
 • የዳይሬክቶሬቱን ስትራቴጂካዊ ግቦችን ለማሳካት የሚያስፈልጉ ግብአቶችን የሰለጠነ ባለሙያና ድጋፍ ሰጪ የሰው ሀይል በቅጥር፣ በእድገት ወይም በዝውውር እንዲሁም አስፈላጊ ሎጂስቲክ የሚሟላበትን ሁኔታዎች ያመቻቻል፣  ለሚመለከተው አካል ጥያቄ  በማቅረብ ተግባራዊ እንዲሆን ያደርጋል፤
 • ከመንግስት ወይም ከኤጀንሲው የሚወጡ ፖሊሲዎችን፣ ስትራቴጂዎች፣ አዋጆች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎችና የተለያዩ ማንዋሎች መተግበራቸውን ይከታተላል፤
 • ስለ ዳይሬክቶሬቱ አጠቃላይ የሥራ አፈጻጸም ወቅታዊ ሪፖርት ለሚመለከተው ለሚመለከተው የስራ ክፍል ያቀርባል፤
 • ለውጥና መልካም አስተዳደር ስራዎች ለተቋሙ ተልዕኮ ስኬት እንዲያግዙ የሚረዱ ስራዎችን ይሰራል፤
 • የዳሬክቶሬቱን ሠራተኞች የሥራ አፈጻፀም መገምገም፤ ግብረ-መልስ መስጠት እንዲሁም አስፈላጊ ሥልጠናዎችን በመስጠት ወይም እንዲሰጥ በማድረግ አቅማቸውን ይገነባል፤ ብቃታቸውን ያረጋግጣል፤
 • በቴክኖሎጂ የተደገፈ ዘመናዊ አሰራር ስርዓት የሚዘረጋበትን አሰራር ይቀይሳል፣ ያቅዳል፣ ይተገብራል እንዲሁም ያስፋፋል፤
 • በዳይሬክቶሬቱ ባለሙያዎች መካከል የተጠናከረ እና ተመጋጋቢነት ያለው ግንኙነት የተቀናጀ አሰራር ይዘረጋል፣ መፈፀሙን ያረጋግጣል፤
 • መመሪያዎችንና አሰራሮችን በየጊዜው እንዲፈተሹና እንዲሻሻሉ ሀሳብ/ግብዓት ያቀርባል በወቅቱ እንዲፈቱ ያደርጋል፤
 • በአፈጻጸም ሂደት የተገኙ ተሞክሮዎችን በመቀመር ወይም እንዲቀመር በማድረግ የማስፋት ሥራን ይሰራል፤
 • ከስራው ጋር ተያያዥነት ያላቸውን አጠቃላይ መረጃዎች ይሰበስባል፣ ይይዛል እና  ለሚመለከታቸው ካላት ያስተላልፋል፤
 • የሚዘጉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን ንብረት የማጣራት ስራዎችን ይፈጽማል፤ ይከታተላል፣
 • ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የሚቀርቡ የንብረት ይወገድልን ወይም ይተላለፍልን ጥያቄ ከቀረበ በጥያቄው መሰረት ንብረት ይቆጥራል፤ ሰነዶችን ይመረምራል፤ ንብረቶቹ በአግባቡ ያደራጃል፤
 • የተዘጉ ድርጅቶችን ንብረት በሚጣራበት ወቅት ወጪዎቹ በትክክል ኦዲት ስለመደረጉ ጥርጣሬ የሚያሳድር ሆኖ ከተገኘ በኤጀንሲው ኦዲተር ተሹሞ እንዲመረመር የውሳኔ ሃሳብ ያቀርባል፤
 • የተመዘበሩና ከአላማቸው ውጪ የተጠቀሙበት ሀብት መኖሩን ከተረጋገጠም መረጃዎችን ያደራጃል፣የተዘጉ ድርጅቶችን ንብረት  እዳና እገዳ ያለመኖራቸውን በጋዜጣ እንዲወጣና እንዲረጋገጥ ያደርጋል፣
 • በሚዘጉ የድርጅቶች አመራሮች ሲሰሩበት የነበረውን የህዝብ ንብረት በአግባቡ አስረክበው ማጠናቀቃቸውን በማረጋገጥ ክሊራንስ ያዘጋጃል፣
 • በማጣራት፣ በማስተላለፍና በማስወገድ ሂደት የወጡ ወጪዎችን በመመሪያ መሰረት እንዲተኩ ያደርጋል፣
 • የተዘጉ ድርጅቶች ንብረት ወይም በስራ ላይ ያሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ለኤጀንሲው በፍቃዳቸው የይወገድልን/ይተላለፍልን ጥያቄ ሲያቀርቡ በአዋጁ መሰረት እንዲተላለፍ/እንዲወገድ የውሳኔ ሃሳብ ያቀርባል፣ ሲፀድቅ ይፈጽማል፣
 • የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈ እና ወደ ሌላ አካል ሊተላለፉ የማይችሉ  የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችንብረቶችን በህጉ መሰረት እንዲያቃጥሉ ወይም በመቅበር እንዲያስወግዱ ድጋፍ ያደርዳል፤
 • እዳ ያለባቸው የተዘጉ ድርጅቶችን ንብረት ሰብስበው ለሌላ አካል መተላለፍ የማይችሉ ግን ቢሸጡ ዋጋ የሚያወጡ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ንብረት በጨረታ ለመሸጥ የንብረቶቹን የገበያ ዋጋ ግምት ያወጣል፣ ከአቅሙ በላይ የሆኑ ወይም ልዩ ሙያ የሚያስፈልጉትን የሙያ እገዛ ጥያቄ ለቡድን መሪው ያቀርባል፤
 • የንብረት ሽያጭ ጨረታ ሰነድ ያዘጋጃል፣ በጨረታ  አወጣጥ ሂደት ላይ በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋባዥነት ተሳታፊ ይሆናል፣
 • የጨረታ ተወዳዳሪዎችን ትንተና የማመዛዘን ስራ ይሰራል፣ ለጨረታ አጽዳቂ ኮሚቴ የውሳኔ ሃሳብ ያቀርባል፣
 • የተዘጉ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችአመራሮች ሲሰሩበት የነበረውን የህዝብ ንብረት በአግባቡ አስረክበው ማጠናቀቃቸውን በማረጋገጥ ክሊራንስ አዘጋጅቶ ያቀርባል፣
 • የሚሸጡ ንብረቶችን የቀረጥ ነፃ መጠቀሚያ መብት ጊዜ ማለፉንና አለማለፉን የማረጋገጥ ተግባር ይመረምራል፣
 • የባለመብቶችን የይገባኛል ጥያቄ መርምሮ ለቡድን መሪው ወይም ለዳይሬክቶሬቱ የውሳኔ ሃሳብ ያቀርባል፣
 • የንብረት ማጣራት፤ ማስተላለፍና ማስወገድ ስራ ቀልጣፋ ለማድረግና የሚያጋጥሙትን ችግሮች ለመፍታት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር  በመቀናጀት ይሠራል፤