አገልግሎቶች

ስትራቴጂክ አጋርነትና ትብብር መመስረት

  • የሲቪል ማኀበረሰብ ድርጅቶች የስትራቴጂክ አጋርነትና ትብብር መመሪያ፣ የአሰራር ማኑዋሎች፣ ቅፃቅፆች እና ቼክሊስቶችን ሲዘጋጁ ይሳተፋል፣ ለሚመለከተውለውሳኔ ያቀርባል፣ ሲፈቀድም ስልጠና እንዲሰጥና፣ ስራ ላይ እንዲውል ያደርጋል፣
  • አዋጁን፤ ደንቡን፤ መመሪያዎችንና የስትራቴጂክ አጋርነትና ትብብር አሰራርን በመፈተሽ አዳዲስ አሰራሮችን ችግሮች እንዲፈቱ የ¥ššÃhúïCN ያቀርባል፣
  • የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን አሰራር ህግ ጥሰት ጥቆማ ኤጀንሲው ከዘርፍ አስተዳደሮችና ክልል መንግስታት ጋር በጋራ የክትትልና፣ ቁጥጥርና ምርመራቅንጅታዊ አሰራሮች ማንዋሎችንና ስምምነቶችን ያዘጋጃል፤
  • በሀገር አቀፍ እና በአለም አቀፍ ከሚገኙ ባለድርሻና ተባባሪ አካላት ጋር በጋራ የሚሰሩ ተግባራትን የአፈጻጸም ደረጃ በአካል ተገኝቶ ይገመግማል፣ የታዩክፍተቶችን ለይቶ ያቀርባል፣
  • በሀገር አቀፍ እና በአለም አቀፍ ከሚገኙ ባለድርሻና ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር ቀጣይነት ያለው የአሰራር ስርአት እንዲዘረጋ ከሚመለከተዉ አካል ጋርተቀናጅቶ ይሰራል፤
  • በሀገር አቀፍ እና በአለም አቀፍ ከሚገኙ ባለ ድርሻና ተባባሪ አካላት ጋር በሚደረጉ ግንኙነቶች በተለዩ ክፍተቶች ዙሪያ ተቀባይነት ያገኙት የመፍትሄ ሃሳቦችተግባራዊ እንዲሆኑ ያደርጋል፤
  • ኤጀንሲው ከአለም አቀፍ ድርጅቶችና አገር አቀፍ ድርጅቶችን መልካም የስራ ግንኙነት እና አጋርነትን እንዲኖር ሁኔታዎች ያመቻቻል፤
  • ከአጋር አካላት በተገኙ ሃብቶች ድጋፍ የሚከናወኑ ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ ግብረ መልስ ይሰጣል፤