በምዝገባ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት የሚሰጡ አገልግሎቶች
 • የሚዘጉ ድርጅቶችን እንደአግባቡ መርምሮ የውሳኔ ሀሳብ ማቅረብና የመዝጊያ ደብዳቤ አዘጋጅቶ ማቅረብ፤
 • ጥቆማዎችን መቀበል፣ ማጥራት፣ሪፖርት ማዘጋጀትና ግብረ መልስ መስጠት፤
 • የፕሮጄክት መገምገም እና ግብረ-መልስ መስጠት፤
 • በጠቅላላ ጉባዔ /ቦርድ መር ስብሰባ ላይ በመገኘት የድጋፍ አገልግሎት መስጠት፤
 • ለባንክ የድጋፍ ደብዳቤ መስጠት/አዲስ ባንክ የፈራሚ ለውጥ፤
 • ለባንክ የድጋፍ ደብዳቤ መስጠት የሚዘጋ ባንክ፤
 • የሥራ ፈቃድ የድጋፍ ደብዳቤ መስጠት፤
 • የሥራ ፈቃድ የድጋፍ ደብዳቤ መስጠት /እድሳት/፤
 • ከቀረጥ ነፃ የድጋፍ ደብዳቤ፤
 • ኮድ 35 ሰሌዳ የድጋፍ ደብዳቤ መስጠት፤
 • ከቫት ተመላሽ ድጋፍ መስጠት፤
 • ለሚመለከተው መስሪያ ቤት አሳውቁልኝ እና የድጋፍ ደብዳቤ፤
 • የገቢ ማስገኛ ስራ ለመስራት፤
 • የሕዝባዊ መዋጮ ማሰባሰብ ስራ፤
 • አመታዊ የስራ ክንውን ሪፖርት፣ ኦዲት ሪፖርትና ግብረመልስ፤
 • የመስክ ክትትልና ግብረመልስ፤
 • የዴስክ ክትትልና ግብረመልስ፤
 • ምርመራ፤
የምዝገባና ሰነድ ማረጋገጥ ቡድን አገልግሎቶች
 • ለአዲስ የሲቪል ማህበረሰብ ተመዘጋቢ ድርጅቶች የምዘገባ ሰርተፊኬት ማዘጋጀት/ መስጠት፤
 • የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ስያሜ በጋዜጣ ማሳወጃ ደብዳቤ መስጠት፤
 • የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አርማ/ሎጎ ማሳወጃ ደብዳቤ መስጠት አዲስ ለተመዘገቡ ድርጅቶች የመጀመሪያ ባንክ ሂሳብ እንዲከፍቱ ደብዳቤ ማዘጋጀት፤
 • የስያሜ ለውጥ መስጠት፤
 • የጠፋ ሰርተፍኬት ምትክ መስጠት፤
 • መተዳደሪያ ደንብ ማሻሻያ መገምገም፤
 • የሲቪልማህበረሰብ ድርጅቶች አደረጃጀትመቀየር፣መዋሃድ፣ መከፈል አገልግሎት መስጠት፤
 • በጎ አድራጎት ኮሚቴ መመዝገብ፤
 • ለሰነዶች ማረጋገጫ የስራ አስኪያጅ እና የስራ መሪዎች ማሳወቅ አገልግሎት መስጠት፤
 • የሰነድ ትክክለኛ ቅጂ መስጠት፤
 • መረጃ መስጠት በሲዲ/በሀርድ ኮፒ፤
 • የደረሰኝ ህትመት አገልግሎት የድጋፍ ደብዳቤ መጻፍ፤
 • የሰርተፊኬት ፣ የምዝገባ ደብዳቤ እና መተዳደሪያ ደንብ ማረጋገጥ አገልግሎት፤
 • ለሚመለከተው መስሪያ ቤት አሳውቁልኝ እና የድጋፍ ደብዳቤ፤
 • ለሀገር ተወካይ/ሪጅናል ተወካይ የመጀመሪያ የስራ ፈቃድ የድጋፍ ደብዳቤ፤
የምዝገባ፣ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ስልጣንና ተግባር
 • በዚህ አዋጅ መሠረት ድርጅቶችን መመዝገብ፣ መደገፍ፣ሥራቸውን ማሳለጥና ማስተባበር፤
 • ድርጅቶች ሥራቸውን በሕግ አግባብ ማከናወናቸውንለማረጋገጥ አስፈላጊውን ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ፤
 • የድርጅቶችን ዓመታዊ የሥራና የገንዘብ እንቅስቃሴ ሪፖርት በዚህ ሕግ በተወሰነው መሠረት መመርመር፤
 • ድርጅቶች ግልጽነትና ተጠያቂነትን የሚያረጋግጥ የውስጥ አስተዳደር እና የራስ አስተዳደር ሥርዓት እንዲኖራቸው አስፈላጊውን ድጋፍ መስጠትና ተፈፃሚነቱን መከታተል፤
 • አግባብነት ባላቸው ሕጎች ስለሰነዶች ማረጋገጥና ምዝገባ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ የድርጅቶችን መተዳደሪያ ደንቦችና ማሻሻያዎቻቸውን ማረጋገጥና መመዝገብ፤